ምሳሌ 23:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም “ተደብድቤአለሁ፤ ነገር ግን አልተጐዳሁም፤ ተመትቼአለሁ፤ ሕመሙ ግን አልተሰማኝም፤ መቼ ነው የምነቃው? ሌላ ተጨማሪ መጠጥ የምጠጣው መቼ ይሆን?” ትላለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተም፣ “መቱኝ፤ አልተጐዳሁም፤ ደበደቡኝ፤ አልተሰማኝም፤ ታዲያ፣ ሌላ መጠጥ እንዳገኝ፣ መቼ ነው የምነቃው?” ትላለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መቱኝ፥ ያውም አልተሰማኝም፥ ደበደቡኝ፥ አላወቅሁምም። መቼ እነሣለሁ? ደግሞ ጨምሬ እፈልጋለሁ ትላለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “መቱኝ፥ ያውም አልተሰማኝም፤ ዘበቱብኝ፥ እኔም አላወቅሁም። ከእኔ ጋር የሚሄዱትን መጥቼ እፈልግ ዘንድ መቼ ጧት ይሆናል?” ትላለህ። |
እናንተ ግን ጥሪውን በመቀበል ፈንታ በዓል አደረጋችሁ፤ የምትበሉትንም በግና በሬ ዐረዳችሁ፤ ወይን ጠጅም ጠጥታችሁ “ነገ እንሞታለን ዛሬ እንብላ እንጠጣ!” አላችሁ።
“የእስራኤል ሕዝብ በሐዘን እንዲህ ሲሉ ሰማኋቸው፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ! እኛ እንዳልተገራ ወይፈን ነበርን፤ አንተ ግን መታዘዝን አስተማርከን፤ አንተ አምላካችን ስለ ሆንክ አሁንም ወደ አንተ ወደ አምላካችን መልሰን፤ እኛም እንመለሳለን።
እግዚአብሔር ሆይ ዐይኖችህ እውነትን የሚመለከቱ አይደሉምን? አንተ ቀሠፍሃቸው፤ እነርሱ ግን ከምንም አልቈጠሩትም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ከስሕተታቸው መማር እምቢ አሉ፤ እልኸኝነትን አበዙ እንጂ፥ ከኃጢአታቸው መመለስ አልፈለጉም።
እንደዚህ ያለው ሰው የዚህን ርግማን ቃላት ሰምቶ ምንም እንኳ በራሴ መንገድ ብቀጥል እኔ እድናለሁ ብሎ በልቡ ቢያስብ በደጎችና በክፉዎች ሰዎች ላይ ጥፋትን ያመጣል።
“የተፋውን ለመዋጥ ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል።” እንዲሁም “ዐሣማ ከታጠበ በኋላ ተመልሶ በጭቃ ላይ ይንከባለላል” የሚለው እውነተኛ ምሳሌ ደርሶባቸዋል።