የአስተዋይ ሰው ልብ ጥበብን የተሞላ ነው፤ በሞኞች ልብ ግን ጥበብ አትታወቅም።
ጥበብ በአስተዋዮች ልብ ታድራለች፤ በሞኞች መካከል እንኳ ራሷን ትገልጣለች።
በአዋቂ ልብ ጥበብ ትቀመጣለች፥ በሰነፎች ውስጥ ግን አትታወቅም።
በደግ ሰው ልብ ጥበብ ታድራለች፤ በአላዋቂ ሰው ልብ ግን አትታወቅም።
የሞኝ ቊጣ ወዲያው ይታወቃል፤ ብልኅ ሰው ግን በእርሱ ላይ የተሰነዘረውን ስድብ ችላ ይላል።
አስተዋይ ሰዎች “ዐዋቂዎች ነን” እያሉ አይመጻደቁም፤ ሞኞች ግን “ዐዋቂዎች ነን” በማለት ድንቊርናቸውን ይገልጣሉ።
አስተዋይ ሰዎች ለሚሠሩት ሥራ አስቀድመው ዕቅድ ያወጣሉ፤ ማስተዋል የጐደላቸው ሰዎች ግን አላዋቂነታቸውን ይገልጣሉ።
ችግር ሲመጣ ክፉዎች ይወድቃሉ፤ ጻድቃን ግን በታማኝነታቸው ይጠበቃሉ።
እውነተኛነት አንድን ሕዝብ ታላቅ ያደርገዋል፤ ኃጢአት ግን ማንኛውንም ሕዝብ ያዋርዳል።
የጠቢባን አንደበት ዕውቀትን ያፈልቃል። የሞኞች አፍ ግን ሞኝነትን ይለፈልፋል።
ደጋግ ሰዎች ከመናገራቸው በፊት ያስባሉ፤ ክፉዎች ግን በችኰላ ክፉ ቃል ይናገራሉ።
ጠቢብ ትሆናለህ፤ ዕውቀትም ደስታን ይሰጥሃል።
ሞኝ ሰው የቊጣ ስሜቱን ይገልጣል፤ ጥበበኛ ሰው ግን ቊጣውን በትዕግሥት ይገታል።
ሞኝ ሰው በሚተላለፍበት መንገድ ሁሉ ያለ ሐሳብ ይራመዳል፤ ለሰውም ሁሉ ሞኝነቱን ያሳውቃል።