አብድዩ 1:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በዚያን ጊዜ ከኤዶም ጥበበኞችን፥ ከዔሳው ተራራ ዕውቀትን አጠፋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዚያ ቀን ጥበበኛ ሰዎችን ከኤዶም፣ አስተዋዮችንም ከዔሳው ተራሮች አልደመስስምን?” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ ቀን ከኤዶምያስ ጥበበኞችን፥ ከዔሳውም ተራራ ማስተዋልን አላጠፋምን? ይላል ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ቀን ከኤዶምያስ ጥበበኞችን፥ ከዔሳው ተራራም ማስተዋልን አጠፋለሁ ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያ ቀን ከኤዶምያስ ጥበበኞችን፥ ከዔሳውም ተራራ ማስተዋልን አላጠፋምን? ይላል እግዚአብሔር። |
በጾዓን ያሉ የንጉሡ ባለ ሥልጣኖች ፍጹም ሞኞች ናቸው፤ ጠቢባን የሆኑት የግብጽ ንጉሥ አማካሪዎች ጥቅም የሌለው ምክር ይመክራሉ፤ እንዴት አድርገው ለንጉሡ “እኛ ብልኆች ነን፤ ዘራችንም ከቀድሞ ነገሥታት ሲወርድ፥ ሲዋረድ የመጣ ነው” ይላሉ?
ግብጻውያን ተስፋ ይቈርጣሉ፤ ዕቅዳቸውም ተግባራዊ እንዳይሆን አደርጋለሁ፤ በዚህም ጊዜ እንዲረዱአቸው ጣዖቶቻቸውን ይጠይቃሉ፤ ሙታንን ወደሚጠሩ ጠንቋዮቻቸው ሄደው ይማከራሉ፤ ከሙታን መናፍስትም ምክር ይጠይቃሉ።
አስደናቂ ተአምርን አከታትዬ በማምጣት ይህ ሕዝብ እንዲገረም አደርገዋለሁ፤ የጥበበኞች ጥበብ ትሰወራለች፤ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትረሳለች።”