አብድዩ 1:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በችግራቸው ቀን ወደ ሕዝቤ በር ልትገባ ባልተገባህ ነበር፤ በመከራቸውም ቀን በይሁዳ ሕዝብ ጥፋት ለመደሰት መተባበር አይገባህም ነበር፤ በመጥፊያቸው ቀን የእነርሱን ንብረት መዝረፍ ባልተገባህም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጥፋታቸው ቀን፣ በሕዝቤ በር መግባት የለብህም ነበር፤ በጥፋታቸው ቀን፣ በጭንቀታቸው መደሰት አልነበረብህም፤ በጥፋታቸው ቀን፣ ሀብታቸውን መዝረፍ አይገባህም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጥፋታቸውም ቀን በሕዝቤ በር ልትገባ፥ በጥፋታቸውም ቀን መከራቸውን ልትመለከት፥ በጥፋታቸውም ቀን በሀብታቸው ላይ እጅህን ልትዘረጋ አይገባህም ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በችግራቸውም ቀን በሕዝቤ በር ትገባ ዘንድ፥ በጥፋታቸውም ቀን ጉባኤያቸውን ትመለከት ዘንድ፥ በእልቂታቸውም ቀን በሠራዊታቸው ላይ አደጋ ትጥል ዘንድ አይገባህም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጥፋታቸውም ቀን በሕዝቤ በር ትገባ ዘንድ፥ በጥፋታቸውም ቀን መከራቸውን ትመለከት ዘንድ፥ በጥፋታቸውም ቀን በሀብታቸው ላይ እጅህን ትዘረጋ ዘንድ አይገባህም ነበር። |
ቅጥረኞች ወታደሮችዋም እንደ ሰቡ ወይፈኖች ናቸው፤ ወደ ኋላ ተመልሰው ይሸሻሉ፤ የፍርድና የጥፋት ቀን ስለ ደረሰባቸው፥ ጸንተው መዋጋት አይችሉም።
“ ‘እኔ እግዚአብሔር እዚያ ያለሁ ብሆንም እንኳ ሁለቱን ሕዝቦች፥ ማለት ይሁዳንና እስራኤልን፥ እንዲሁም ምድራቸውን ጭምር የእናንተ አድርጋችሁ ለመውረስ አስባችሁ ነበር።
“ ‘ለብዙ ጊዜ ከቈየው ጥላቻችሁ የተነሣ በኃጢአቱ ምክንያት በደረሰበት የመጨረሻ ቅጣትና በመከራው ጊዜ የእስራኤልን ሕዝብ ለሰይፍ አሳልፋችሁ ሰጣችሁ።
“ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ብለህ ለእስራኤል ተራራዎች ትንቢት ተናገር አለኝ፦ የባዕድ አገር ሕዝቦች በሁሉም አቅጣጫ ምድራችሁን ስላፈራረሱትና በእርግጥም ባድማ ስላደረጉት አገራችሁ ለሌሎች ሕዝቦች ንብረት ሆነ። እናንተም የሰዎች መሳቂያና መሳለቂያ ሆናችኋል።
ሰላም አግኝተው በጸጥታ በሚኖሩ በአሕዛብ መንግሥታት ላይ እጅግ ተቈጥቼአለሁ፤ ምክንያቱም እኔ ሕዝቤን ከመቅጣት መለስ ባልኩበት ጊዜ እነዚያ የአሕዛብ መንግሥታት ሕዝቤን ከተጠበቀው በላይ አሠቃይተዋል።