ሌሎች የሌዋውያን ቤተሰቦች አለቆች መዘምራን ነበሩ፤ እነርሱ ሌት ተቀን የማገልገል ኀላፊነት ስለ ነበረባቸው ከሌሎች አገልግሎቶች ነጻ በመሆን በቤተ መቅደሱ ቅጽር ግቢ በተዘጋጁላቸው ክፍሎች ውስጥ ይኖሩ ነበር።
ነህምያ 12:46 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከንጉሥ ዳዊትና የመዘምራን አለቃ ከነበረው አሳፍ ዘመንም ጀምሮ ለመዘምራንና ለማኅሌታዊ ዜማ መሪዎች ነበሩአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀድሞ በዳዊትና በአሳፍ ዘመን ለእግዚአብሔር የሚቀርቡትን የውዳሴ መዝሙሮችና ምስጋና የሚመሩ የመዘምራን አለቆች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አስቀድሞም በዳዊትና በአሳፍ ዘመን እግዚአብሔርን በዜማ ለማመስገንና ለማክበር የመዘምራን አለቆች ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዳዊትም ዘመን አሳፍ የመዘምራን አለቃ ነበር፤ እነርሱም እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አስቀድሞም በዳዊትና በአሳፍ ዘመን እግዚአብሔርን በዜማ ለማመስገንና ለማክበር የመዘምራን አለቆች ነበሩ። |
ሌሎች የሌዋውያን ቤተሰቦች አለቆች መዘምራን ነበሩ፤ እነርሱ ሌት ተቀን የማገልገል ኀላፊነት ስለ ነበረባቸው ከሌሎች አገልግሎቶች ነጻ በመሆን በቤተ መቅደሱ ቅጽር ግቢ በተዘጋጁላቸው ክፍሎች ውስጥ ይኖሩ ነበር።
ንጉሡና የሕዝቡ መሪዎች ሁሉ በዳዊትና በነቢዩ አሳፍ የተደረሱትን የምስጋና መዝሙሮች ለእግዚአብሔር ክብር እንዲዘምሩ ሌዋውያንን አዘዙ፤ ስለዚህ ሁሉም ተንበርክከው በመስገድ ላይ ሳሉ በታላቅ ደስታ ይዘምሩ ነበር።
ማታንያ የሚካ ልጅ፥ የዘብዲ ልጅ፥ የመዘምራን አለቃ የነበረው የአሳፍ ልጅ፥ የእርሱ ምክትል የነበረው የባቅቡቅያ ልጅና፥ የሻሙዐ ልጅ የነበረው ዐብዳ፥ የጋላል ልጅ፥ የዩዱቱን ልጅ፥