ሚክያስ 6:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እህል ትዘራላችሁ ሰብል ግን አትሰበስቡም፤ የወይራ ፍሬ ትጨምቃላችሁ፤ ነገር ግን በዘይቱ አትጠቀሙም፤ የወይን ፍሬ ትጨምቃላችሁ፤ የወይን ጠጅ ግን አትጠጡም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትዘራለህ፤ ነገር ግን አታጭድም፤ የወይራ ዘይት ትጨምቃለህ፤ ነገር ግን ዘይቱን አትቀባም፤ ወይንን ትቈርጣለህ፤ ነገር ግን የወይን ጠጅ አትጠጣም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትዘራለህ፥ ነገር ግን አታጭድም፤ ወይራ ትጨምቃለህ፥ ነገር ግን ዘይቱን አትቀባም፤ ወይን ትጨምቃለህ፥ ነገር ግን የወይን ጠጁን አትጠጣም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትዘራለህ፥ ነገር ግን አታጭድም፥ ወይራውንም ትጨምቃለህ፥ ነገር ግን ዘይቱን አትቀባም፥ ወይኑንም ትጨምቃለህ፥ ነገር ግን የወይን ጠጁን አትጠጣም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትዘራለህ፥ ነገር ግን አታጭድም፥ ወይራውንም ትጨምቃለህ፥ ነገር ግን ዘይቱን አትቀባም፥ ወይኑንም ትጨምቃለህ፥ ነገር ግን የወይን ጠጁን አትጠጣም። |
የሚከተለውን አመጣባችኋለሁ፦ ታላቅ ድንጋጤን፥ ክሳትን፥ ዐይንን የሚያፈዝና ሰውነትን የሚያመነምን የንዳድ በሽታ አመጣባችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁ የሚበሉት ስለ ሆነ ዘራችሁን በከንቱ ትዘራላችሁ።
ድኾችን ጨቊናችሁ፤ እህላቸውንም አስገብራችሁ፤ ከጥርብ ድንጋይ ቤቶች ሠርታችኋል፤ እናንተ ግን አትኖሩባቸውም፤ የሚያስደስት ወይን ተክላችኋል፤ ነገር ግን ከእርሱ የሚገኘውን የወይን ጠጅ እናንተ አትጠጡም።
ምንም እንኳ የበለስ ዛፍ ባያብብ፥ በወይን ተክል ላይም ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ዛፍም ምንም ፍሬ ባይሰጥ፥ በእርሻዎች ላይ ሰብል ቢጠፋ፥ የበግ መንጋዎች ሁሉ ቢያልቁ፥ በበረት ውስጥ ምንም ከብት ባይገኝ፥
ሀብታቸው ይዘረፋል፤ ቤቶቻቸውም ይፈርሳሉ፤ በዚያን ጊዜ ቤት ይሠራሉ፤ ነገር ግን አይኖሩበትም፤ ወይንም ይተክላሉ፤ ነገር ግን የወይኑን ጠጅ አይጠጡም።”
እነሆ ብዙ ዘርታችሁ ጥቂት ሰበሰባችሁ፤ ትበላላችሁ፤ ነገር ግን አትጠግቡም፤ ትጠጣላችሁ፤ ነገር ግን አትረኩም፤ ደራርባችሁ ትለብሳላችሁ፤ ነገር ግን አይሞቃችሁም፤ ሠርታችሁ የምታገኙት ደመወዝ ስለማይበረክትላችሁ፥ በቀዳዳ ኪስ ውስጥ የማኖር ያኽል ይሆናል።
በአገሪቱ ላይ በመስፈር በጋዛ ዙሪያ እስካለው ስፍራ ድረስ የምድሪቱን ሰብል ያጠፉ ነበር፤ የበግ፥ የከብትና የአህያ መንጋቸውንም እየነዱ ስለሚወስዱባቸው ለእስራኤላውያን ምንም ነገር አያስቀሩላቸውም ነበር።