ዘሌዋውያን 27:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባለ ንብረቱ እንስሶቹ በየዐይነቱ በሚመድብበት ጊዜ ነውረኛውን ከደኅነኛው አይለይ፤ በእርሱም ሌላ ምትክ አያድርግ። በአንዱ እንስሳ ሌላ እንስሳ ተክቶ ቢገኝ ግን፥ ሁለቱም እንስሶች ለእግዚአብሔር የተለዩ ይሁኑ፤ እንደገና መዋጀትም የለባቸውም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውየው መልካም የሆነውን መልካም ካልሆነው አይለይ ወይም አይተካ፤ አንዱን በሌላው ቢተካ ግን ሁለቱም እንስሳት የተቀደሱ ይሆናሉ፤ ሊዋጁም አይችሉም።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልካም ወይም መጥፎ እንደሆነ አይመርምር፥ አይለውጥም፤ ቢለውጠውም እርሱና ልዋጩ ሁለቱም የተቀደሱ ይሆናሉ፤ አይቤዥም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልካሙን በክፉ፥ ክፉውንም በመልካም አይለውጥ፤ ቢለውጠውም እርሱና ልዋጩ የተቀደሱ ይሆናሉ፤ አይቤዠውም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልካም ወይም ክፉ እንዲሆን አይመርምር፥ አይለውጥም፤ ቢለውጠውም እርሱና ልዋጩ የተቀደሱ ይሆናሉ፤ አይቤዠውም። |
በዚያን ቀን ሰዎች ያፌዙባችኋል፤ እንዲህም እያሉ የምፀት ሙሾ ያወርዱላችኋል፦ “እኛ ፈጽሞ ጠፍተናል! እግዚአብሔር የሕዝባችንን ንብረት ወሰደብን፤ ርስታችንንም ለማራኪዎቻችን አከፋፈለ።”