“መቼም በደል የማይሠራ የለምና ሕዝብህ ኃጢአት በመሥራት አንተን ሲያሳዝኑህ፥ አንተም ተቈጥተህ ጠላቶቻቸው ድል እንዲነሡአቸውና ወደ ሌላ አገር ማርከው እንዲወስዱአቸው በምትፈቅድበት ጊዜ፥ ምንም እንኳ ያ አገር ሩቅ ቢሆን፥
ዘሌዋውያን 26:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእናንተም ላይ ጦርነት አምጥቼ በባዕዳን አገሮች ሁሉ እበትናችኋለሁ፤ ሰይፍንም አስመዝዝባችኋለሁ፤ ምድራችሁ ሰው አልባ፥ ከተሞቻችሁም ውድማ ይሆናሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤ ሰይፌን መዝዤም አሳድዳችኋለሁ። ምድራችሁ ባድማ፣ ከተሞቻችሁም ፍርስራሽ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተንም በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፥ ሰይፍንም አስመዝዝባችኋለሁ፤ ምድራችሁም ባድማ ትሆናለች፥ ከተሞቻችሁም ይፈርሳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተንም በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤ በሄዳችሁበትም ሁሉ ሰይፍ ታጠፋችኋለች፤ ምድራችሁም የተፈታች ትሆናለች፤ ከተሞቻችሁም ባድማ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተም ከአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፥ ሰይፍንም አስመዝዝባችኋለሁ፤ ምድራችሁም የተፈታች ትሆናለች፥ ከተሞቻችሁም ባድማ ይሆናሉ። |
“መቼም በደል የማይሠራ የለምና ሕዝብህ ኃጢአት በመሥራት አንተን ሲያሳዝኑህ፥ አንተም ተቈጥተህ ጠላቶቻቸው ድል እንዲነሡአቸውና ወደ ሌላ አገር ማርከው እንዲወስዱአቸው በምትፈቅድበት ጊዜ፥ ምንም እንኳ ያ አገር ሩቅ ቢሆን፥
እርሱም ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የታላላቅ ሰዎችን ቤቶችና በከተማው ውስጥ የሚገኙትንም ሌሎች ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤
እነርሱም “ተማርከው ወደ ባቢሎን ሳይወሰዱ የቀሩትና በሕይወት ያሉት አይሁድ በታላቅ ችግርና ኀፍረት ላይ ወድቀው ይገኛሉ፤ የኢየሩሳሌምም ቅጽሮች ፈራርሰው ወድቀዋል፤ የቅጽር በሮቹም በእሳት ጋይተዋል” ሲሉ መለሱልኝ።
‘እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እኔን በእምነት ባትከተሉ በአረማውያን ሕዝቦች መካከል እበትናችኋለሁ፤ ነገር ግን ወደ እኔ ተመልሳችሁ ያዘዝኳችሁን ትእዛዞች ብትፈጽሙ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ የተበታተናችሁ ብትሆኑም እንኳ ለስሜ መጠሪያ እንዲሆን ወደ መረጥሁት ስፍራ እንደገና በመሰብሰብ መልሼ አመጣችኋለሁ’ ስትል ለሙሴ የተናገርከውን ቃል አስብ።
ስለዚህም ሃማን ለንጉሥ አርጤክስስ እንዲህ ሲል አስረዳው፦ “በንጉሠ ነገሥት መንግሥትህ ግዛት ውስጥ በየአገሩ ተበታትኖ የሚኖር አንድ ሕዝብ አለ፤ ይህም ሕዝብ ከሌሎች አሕዛብ የተለየ ሕግ አለው፤ ከዚህም በላይ ለንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ሕግ ታዛዥ ሆኖ አልተገኘም፤ ታዲያ፥ ይህን ዐይነቱን ሕዝብ ዝም ብለህ ብትታገሥ ለአንተ አደገኛ ነገር ይሆንብሃል፤
እነሆ አገራችሁ ምድረ በዳ ሆናለች፤ ከተሞቻችሁም በእሳት ጋይተዋል፤ የእርሻችሁም ቦታ ዐይናችሁ እያየ የውጪ ጠላት ይወስደዋል፤ ሁሉንም ነገር አጥፍቶ ምድራችሁን ውድማ ያደርጋታል።
እኔም “አቤቱ ጌታ ሆይ፥ ይህ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?” ብዬ ጠየቅሁ። እርሱም “ከተሞች እስኪፈርሱ፥ ቤቶችም የሚኖርባቸው አጥተው ወና እስኪሆኑና አገሪቱም የተፈታች ባድማ እስክትሆን ድረስ ነው።
የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በይሁዳ በነገሠበት ዘመን በኢየሩሳሌም ስለ ፈጸመው ክፋት ሁሉ በእነርሱ ላይ ከሚደርሰው ነገር የተነሣ የዓለም ሕዝብ እንዲሠቀቅ አደርጋለሁ።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቦች ሆይ! አድምጡኝ፤ በሩቅ ጠረፎችም ቃሌን ዐውጁ፤ እኔ ሕዝቤን በትኜ ነበር፤ አሁን ግን እሰበስባቸዋለሁ፤ እረኛ መንጋውን እንደሚጠብቅም እጠብቃቸዋለሁ።
አንበሳ ከተሸሸገበት ደን እንደሚወጣ፥ ሕዝብን ሁሉ የሚያጠፋ ይነሣል፤ እርሱም ይሁዳን ለማጥፋት ይመጣል፤ የይሁዳ ከተሞች ይፈራርሳሉ፤ የሚኖርባቸውም አይገኝም።
በአንድ ወቅት በሕዝብ ተሞልታ የነበረችው ከተማ እንዴት ብቸኛ ሆነች! በሕዝቦች መካከል ታላቅ የነበረችው እንዴት ባል እንደ ሞተባት ሴት ሆነች! በአውራጃዎች መካከል ልዕልት የነበረችው፥ አሁን እርስዋ እንደ ባሪያ ሆነች።
የይሁዳ ሕዝብ ከጭንቀትና ከከባድ የባርነት ሥራ በኋላ ወደ ምርኮ ተወሰዱ፤ አሁን እነርሱ በሕዝቦች መካከል ሲኖሩ ዕረፍት አያገኙም፤ እነርሱ በጭንቀት ውስጥ እያሉ አሳዳጆቻቸው ደረሱባቸው።
ስለዚህም ሕዝቡ “ወዲያ ሂዱ! ስለ ረከሳችሁም አትንኩን!” እያሉ ይጮኹባቸዋል። ስለዚህ እነርሱ ስደተኞችና ተንከራታቾች ሆኑ ሕዝቦችም “ከእንግዲህ በመካከላችን አይቈዩም” አሉ።
እግዚአብሔር ራሱ የበተናቸው ስለ ሆነ፥ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ እነርሱ አያስብም፤ ለካህናቱ ክብር አይሰጣቸውም፤ ሽማግሌዎችም ልዩ አስተያየት አይደረግላቸውም።
አሁን በሕዝብ ተሞልተው የሚታዩ ከተሞች ይጠፋሉ፤ አገሪቱም ምድረ በዳ ትሆናለች፤ በዚያን ጊዜ እነርሱ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።’ ”
ከበባው ከተፈጸመ በኋላ ከሦስቱ አንዱን እጅ የከተማውን ንድፍ በሠራህበት ጡብ መካከል አቃጥለው፤ ሁለተኛውን አንድ ሦስተኛ እጅ ቈራርጠህ የከተማው ንድፍ በተሠራበት ጡብ ዙሪያ አኑረው። ሦስተኛውን አንድ ሦስተኛ እጅ ደግሞ ለነፋስ በትነው፤ እኔም በሰይፍ አሳድደዋለሁ።
እነሆ ከጥፋት ለማምለጥ ሲሸሹ ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፤ ሜምፊስ ትቀብራቸዋለች፤ ያከማቹት የብር ሀብት ሁሉ ሳማ ለብሶ ይቀራል፤ መኖሪያቸውም እሾኽ ይበቅልበታል።
በጠላቶቻቸው እጅ ተማርከው ቢወሰዱም እዚያ እንዲገደሉ አደርጋለሁ፤ በዚህ ዐይነት እኔ በእነርሱ ላይ የማደርገው ትኲረት ይጐዳቸዋል እንጂ አይጠቅማቸውም።”
እንደ ዐውሎ ነፋስ ጠራርጌ በመውሰድም በማያውቁት ባዕድ አገር እንዲኖሩ አደረግኋቸው፤ ይህችም መልካም ምድር ማንም የማይኖርባት ባድማ ሆና ቀረች፥ ያቺ ያማረች ምድርም ባድማ ሆነች።”
ከእነርሱም ብዙዎች በሰይፍ ይገደላሉ፤ ሌሎችም ተማርከው ወደየአገሩ ይወሰዳሉ። የአሕዛብ ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።”
በዓለም ሁሉ ለተበተኑ ለዐሥራ ሁለቱ ነገዶች የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ከሆነው ከያዕቆብ የተላከ መልእክት፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን።