ባሪያ እንዲሆንህ አንተ በገዛኸው ጊዜ ሚስት ያላገባ ከሆነ፥ ለቆ በሚወጣበት ጊዜ ብቻውን ይሂድ፤ ባሪያው በገዛኸው ጊዜ ሚስት አግብቶ ከሆነ ግን ሚስቱን ይዞ ይውጣ።
ዘሌዋውያን 25:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ዓመት እርሱ ከልጆቹ ጋር ከአንተ ተለይቶ ወደ ወገኖቹና ወደ አባቶቹ ንብረት ይመለሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በኋላ እርሱና ልጆቹ በነጻ ይለቀቁ፤ ወደ ቤተ ሰቡና ወደ አባቶቹ ንብረት ይመለስ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም በኋላ እርሱ ከልጆቹ ጋር ከአንተ ነፃ ይወጣል፥ ወደ ወገኖቹም ወደ አባቱም ርስት ይመለሳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኢዮቤልዩ ዓመትም እርሱ ከልጆቹ ጋር ከአንተ ይወጣል፤ ወደ ወገኖቹም፥ ወደ አባቱም ርስት ይመለሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜም እርሱ ከልጆቹ ጋር ከአንተ ይውጣ፥ ወደ ወገኖቹም ወደ አባቱም ርስት ይመለስ። |
ባሪያ እንዲሆንህ አንተ በገዛኸው ጊዜ ሚስት ያላገባ ከሆነ፥ ለቆ በሚወጣበት ጊዜ ብቻውን ይሂድ፤ ባሪያው በገዛኸው ጊዜ ሚስት አግብቶ ከሆነ ግን ሚስቱን ይዞ ይውጣ።
በዚህም ሁኔታ ኀምሳኛውን ዓመት ለይታችሁ በምድሪቱ ለሚኖሩት ሁሉ ነጻነትን ታውጃላችሁ፤ ከዚያ በፊት የተሸጠ ማናቸውም መሬት ለባለቤቱ ወይም ለዘሩ ይመለሳል፤ ባርያም ሆኖ ለማገልገል የተሸጠ ሰው ወደ ቤተሰቡ ይመለሳል።
ነገር ግን ለመዋጀት የሚያስችል በቂ ገንዘብ ባይኖረው ርስቱ እስከ ተከታዩ የኢዩቤልዩ ዓመት ድረስ በዚያው በገዛው ሰው እጅ ሊቆይለት ይችላል። በዚያም ዓመት ርስቱ ለባለቤቱ ይመለሳል።
ክርስቶስ ከዐመፃ ሁሉ ሊያድነንና መልካም ሥራ ለመሥራት ትጉሆችና ለእርሱ የተለየን ንጹሕ ሕዝብ እንድንሆን ያነጻን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።