ዘሌዋውያን 25:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስከ ተከታዩ የኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ እንደ ተቀጣሪ አገልጋይ እያገለገለህ እንደ መጻተኛ ይኑር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመካከልህ እንዳለ ቅጥር ሠራተኛ ወይም እንደ እንግዳ አድርገህ ቍጠረው፤ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመትም ይሥራልህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይልቁንም እርሱ እንደ ተቀጣሪ አገልጋይ እና እንደ መጻተኛ ከአንተ ጋር ይሁን፤ እስከ ኢዮቤልዩም ዓመት ያገልግልህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ምንደኛና እንደ ስደተኛ ከአንተ ጋር ይሁን፤ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመትም ያገልግልህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ምንደኛና እንደ መጻተኛ ከአንተ ጋር ይሁን፤ እስከ ኢዮቤልዩም ዓመት ያገልግልህ። |
“ወንድም ሆነ ሴት ከእስራኤላውያን ወገን አንድ ሰው ራሱን ባሪያ አድርጎ ለአንተ ቢሸጥልህ፥ ከስድስት ዓመት አገልግሎት በኋላ በሰባተኛው ዓመት ነጻ ታወጣዋለህ፤