“በአንተና በዘርህ፥ በመጪውም ትውልድ መካከል ቃል ኪዳኔን ለዘለዓለም አጸናለሁ፤ በዚህም ዐይነት ለአንተና ከአንተ በኋላ ለሚመጣው ዘርህ አምላክ እሆናለሁ።
ዘሌዋውያን 25:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የከነዓንን ምድር እንድሰጣችሁና አምላካችሁ እንድሆን ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የከነዓንን ምድር ልሰጥህና አምላክህ ልሆን፣ ከግብጽ ያወጣሁህ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የከነዓንን ምድር እንድሰጣችሁ፥ አምላክም እንድሆናችሁ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከነዓንን ምድር እሰጥህ ዘንድ፥ አምላክም እሆንህ ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የከነዓንን ምድር እሰጣችሁ ዘንድ፥ አምላክም እሆናችሁ ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። |
“በአንተና በዘርህ፥ በመጪውም ትውልድ መካከል ቃል ኪዳኔን ለዘለዓለም አጸናለሁ፤ በዚህም ዐይነት ለአንተና ከአንተ በኋላ ለሚመጣው ዘርህ አምላክ እሆናለሁ።
እነሆ ከዚህ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤
አሁን ግን የሚበልጠውን፥ በሰማይ ያለውን አገር ይናፍቃሉ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ከተማን ስላዘጋጀላቸው “አምላካችን” ብለው ቢጠሩት አያሳፍረውም።