ዘሌዋውያን 25:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሊዋጅለት የሚችል የቅርብ ዘመድ ባይኖረው ግን ዘግየት ብሎ ሀብት በሚያገኝበት ጊዜ እርሱ ራሱ መዋጀት ይችላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ሰውየው ርስቱን የሚዋጅለት ምንም ዘመድ ባይኖረውና እርሱ ራሱ መዋጀት የሚችልበትን ሀብት ቢያገኝ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚቤዠውም ሰው ባይኖረው፥ እርሱም ቢበለጥግ፥ ለመቤዠትም የሚበቃ ቢያገኝ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚቤዠውም ሰው ቢያጣ፥ እርሱም እጁ ቢረጥብ፥ ለመቤዠትም የሚበቃ ቢያገኝ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚቤዠውም ሰው ቢያጣ፥ እርሱም እጁ ቢረጥብ፥ ለመቤዠትም የሚበቃ ቢያገኝ፥ |
ይህንንም ማድረግ በሚችልበት ጊዜ እስከ ተከታዩ የንብረት መመለስ ዓመት ያለውን ዘመን ቈጥሮ ቀሪውን ገንዘብ ለገዛው ሰው ከመለሰለት በኋላ ወደ ርስቱ ይመለስ።
“አንድ ሰው በግ ወይም ፍየል ማቅረብ ካልቻለ ግን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች፥ አንደኛይቱን ስለ ኀጢአት ለሚቀርብ መሥዋዕት፥ ሁለተኛይቱንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ የበደሉን ዕዳ ይከፍል ዘንድ ለእግዚአብሔር ያምጣ።