ዘሌዋውያን 25:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከዚያ በፊት የተሸጠ መሬት ሁሉ በዚሁ ዓመት ለባለቤቱ ይመለስለታል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘በዚህ በኢዮቤልዩ ዓመት እያንዳንዱ ሰው ወደ ርስቱ ይመለስ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በዚህ በኢዮቤልዩ ዓመት እያንዳንዱ ሰው ወደ ርስቱ ይመለሳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በዚች ኢዮቤልዩ ዓመት ሰው ሁሉ ወደ ርስቱ ይመለሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚች በኢዮቤልዩ ዓመት ሰው ሁሉ ወደ ርስቱ ይመለሳል። |
ሻጭና ገዢ በሕይወት እስካሉ ድረስ ሻጭ የሸጠውን ዕቃ መልሶ ሊያገኘው እንደማይችል ሁሉ እንዲሁም ራእዩ የተነገረው ስለ ሁሉም ስለ ሆነ ሊታጠፍ አይችልም። እነርሱም ስለ በበደሉ ሕይወታቸውን ማዳን አይችሉም።
በዚህም ሁኔታ ኀምሳኛውን ዓመት ለይታችሁ በምድሪቱ ለሚኖሩት ሁሉ ነጻነትን ታውጃላችሁ፤ ከዚያ በፊት የተሸጠ ማናቸውም መሬት ለባለቤቱ ወይም ለዘሩ ይመለሳል፤ ባርያም ሆኖ ለማገልገል የተሸጠ ሰው ወደ ቤተሰቡ ይመለሳል።
ነገር ግን ለመዋጀት የሚያስችል በቂ ገንዘብ ባይኖረው ርስቱ እስከ ተከታዩ የኢዩቤልዩ ዓመት ድረስ በዚያው በገዛው ሰው እጅ ሊቆይለት ይችላል። በዚያም ዓመት ርስቱ ለባለቤቱ ይመለሳል።
ንብረት በሚመለስበት ዓመት የተሸጠ ንብረት ሁሉ ለባለቤቱ በሚመለስበት ጊዜ የጸሎፍሐድ ሴቶች ልጆች ርስት አግብተው ወደ ሄዱበት ነገድ ለዘለቄታው ተጨማሪ ሆኖ ይተላለፋል፤ ይህም በእኛ ነገድ ይዞታ ላይ ጒድለትን ያስከትላል።”