ዘሌዋውያን 23:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም በመጀመሪያው ቀን ከምድራችሁ ዛፎች ምርጥ ፍሬ፥ የዘንባባ ዝንጣፊና የለምለም ዛፍ ቅርንጫፍ የወንዝ አኻያ ዛፍ ይዛችሁ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት እየተደሰታችሁ እስከ ሰባት ቀን ድረስ በዓል አድርጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመጀመሪያው ቀን የመልካም ዛፍ ፍሬ፣ የዘንባባ ዝንጣፊ፣ የለመለመ ዛፍ ቅርንጫፍ የአኻያ ዛፍ ቅርንጫፍ ይዛችሁ ሰባት ቀን በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመጀመሪያው ቀን የመልካም ዛፍ ፍሬ፥ የዘንባባ ዝንጣፊ፥ የለመለመውን ዛፍ ቅርንጫፍ፥ የወንዝም አኻያ ዛፍ ውሰዱ፤ በአምላካችሁም በጌታ ፊት ሰባት ቀን ደስ ይበላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመጀመሪያዋ ቀን የመልካም ዛፍ ፍሬ፥ የዘንባባውንም ቅርንጫፍ፥ የለመለመውንም ዛፍ ቅርንጫፍ፥ የወንዝም አኻያ ዛፍ ውሰዱ፤ በአምላካችሁም በእግዚአብሔር ፊት በየዓመቱ ሰባት ቀን ደስ ይበላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመጀመሪያው ቀን የመልካም ዛፍ ፍሬ፥ የሰሌን ቅርንጫፍ፥ የለመለመውን ዛፍ ቅርንጫፍ፥ የወንዝም አኻያ ዛፍ ውሰዱ፤ በአምላካችሁም በእግዚአብሔር ፊት ሰባት ቀን ደስ ይበላችሁ። |
እግዚአብሔር የታደጋቸው ሰዎች ተመልሰው ይመጣሉ፤ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘወትር የደስታን ዘውድ ይቀዳጃሉ፤ ተድላና ደስታንም ያገኛሉ፤ ማዘንና መቃተት ከእነርሱ ይርቃል።
“የምድራችሁን መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ ሰባተኛው ወር ከገባ ከዐሥራ አምስተኛው ቀን በመጀመር ይህን የደስታ በዓል በእግዚአብሔር ፊት እስከ ሰባት ቀን ድረስ ታከብራላችሁ፤ መጀመሪያውና ስምንተኛው ቀን ልዩ የዕረፍት ቀን ይሆናል።
እናንተ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆቻችሁ፥ ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮቻችሁ፥ እንዲሁም ከእናንተ ጋር የርስት ክፍያ ከሌላቸው በከተሞቻችሁ ከሚኖሩ ከሌዋውያን ጋር በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ትደሰታላችሁ።
እዚያም በባረካችሁ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት እናንተና ቤተሰቦቻችሁ ሁሉ ተሰብስባችሁ ትበላላችሁ፤ በድካማችሁ ያገኛችሁትን መልካም ነገር ሁሉ ትደሰቱበታላችሁ።
እኛ እግዚአብሔርን በመንፈስ የምናመልክና በውጭ በሚታየው ሥርዓት ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ የምንመካ ስለ ሆንን በእውነት ተገርዘናል።
ኢየሱስ ክርስቶስን ያላያችሁት እንኳ ብትሆኑ ትወዱታላችሁ፤ አሁን እንኳ የማታዩት ብትሆኑ ታምኑበታላችሁ፤ በቃላት ሊገለጥ በማይቻልና በከበረ ደስታ ደስ ይላችኋል።
ከዚህ በኋላ ተመለከትኩ፤ እጅግ ብዙ ሰዎችን አየሁ፤ እነርሱ ከሕዝብና ከነገድ፥ ከወገንና ልዩ ልዩ ቋንቋ ከሚናገሩ ሁሉ የተውጣጡ ነበሩ፤ እነዚህ ነጭ ልብስ ለብሰው፥ የዘንባባ ዝንጣፊ በእጃቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆመው ነበር፤