“የምድራችሁን ሰብል በምትሰበስቡበት ጊዜ የመከር በዓል አክብሩ፤ “ከወይን ተክሎቻችሁና ከፍራፍሬ ዛፎቻችሁ ፍሬ በምትሰበስቡበት ጊዜ በዓመቱ መጨረሻ የዳስ በዓል አክብሩ፤
ዘሌዋውያን 23:39 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የምድራችሁን መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ ሰባተኛው ወር ከገባ ከዐሥራ አምስተኛው ቀን በመጀመር ይህን የደስታ በዓል በእግዚአብሔር ፊት እስከ ሰባት ቀን ድረስ ታከብራላችሁ፤ መጀመሪያውና ስምንተኛው ቀን ልዩ የዕረፍት ቀን ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘የምድራችሁን ፍሬ ከሰበሰባችሁ በኋላ በሰባተኛው ወር ከዐሥራ ዐምስተኛው ቀን ጀምራችሁ ሰባት ቀን ለእግዚአብሔር በዓል አክብሩ፤ የመጀመሪያው ቀን የዕረፍት ዕለት ነው፤ ስምንተኛውም ቀን እንደዚሁ የዕረፍት ዕለት ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በሰባተኛውም ወር በዓሥራ አምስተኛው ቀን የምድሪቱን ምርት በሰበሰባችሁ ጊዜ የጌታን በዓል ሰባት ቀን ጠብቁ፤ በመጀመሪያው ቀን ዕረፍት ይሁን፥ በስምንተኛውም ቀን ዕረፍት ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሰባተኛውም ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን የምድሩን ፍሬ ካከማቻችሁ በኋላ፥ የእግዚአብሔርን በዓል ሰባት ቀን ታደርጋላችሁ፤ የመጀመሪያዋ ቀን ዕረፍት ትሁን፤ ስምንተኛዋም ቀን ዕረፍት ትሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰባተኛውም ወር በአሥራ አምስተኛው ቀን የምድሩን ፍሬ ካከማቻችሁ በኋላ፥ የእግዚአብሔርን በዓል ሰባት ቀን ጠብቁ፤ በመጀመሪያው ቀን ዕረፍት ይሁን፥ በስምንተኛውም ቀን ዕረፍት ይሁን። |
“የምድራችሁን ሰብል በምትሰበስቡበት ጊዜ የመከር በዓል አክብሩ፤ “ከወይን ተክሎቻችሁና ከፍራፍሬ ዛፎቻችሁ ፍሬ በምትሰበስቡበት ጊዜ በዓመቱ መጨረሻ የዳስ በዓል አክብሩ፤
“ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ በሰባተኛው ወር፥ ወሩ በገባ በመጀመሪያው ቀን እግዚአብሔርን ለማምለክ በመለከት የታወጀ መታሰቢያ የዕረፍት ቀን ይሁንላችሁ።
ከሰባቱም ቀኖች በእያንዳንዱ ቀን ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ታቀርባላችሁ፤ በስምንተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ታደርጋላችሁ፤ ለእግዚአብሔርም የሚቃጠል የምግብ መሥዋዕት አቅርቡ፤ ይህም ጉባኤውን የምትፈጽሙበት ቀን ስለ ሆነ ምንም ሥራ አትሥሩበት።
እነዚህም በዓላት ከእግዚአብሔር ሰንበቶች ጋር ተጨማሪ ሆነው የሚከበሩ ናቸው፤ ለእግዚአብሔር ከምትሰጡት ስጦታ ስእለት ሲፈጸምላችሁ ከምትሰጡት ስጦታና በፈቃዳችሁ ከምታቀርቡት ሁሉ ጋር ተደምረው የሚቀርቡ ናቸው።
በዚያም በመጀመሪያው ቀን ከምድራችሁ ዛፎች ምርጥ ፍሬ፥ የዘንባባ ዝንጣፊና የለምለም ዛፍ ቅርንጫፍ የወንዝ አኻያ ዛፍ ይዛችሁ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት እየተደሰታችሁ እስከ ሰባት ቀን ድረስ በዓል አድርጉ።