La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 23:37 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“የምግብ መባ፥ የሚቃጠል መሥዋዕት፥ የእህሉን ቊርባን፥ መሥዋዕቱንና የመጠጡንም ቊርባን፥ በየተወሰነው ቀን ወደ እግዚአብሔር ታቀርቡባቸው ዘንድ የተቀደሱ ስብሰባዎች እንዲሆኑ የምታውጁአቸው የእግዚአብሔር በዓላት እነዚህ ናቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘የሚቃጠል መሥዋዕትንና የእህል ቍርባንን፣ መሥዋዕትንና የመጠጥ ቍርባንን በተመደበላቸው ቀን ለእግዚአብሔር በእሳት ለማቅረብ፣ የተቀደሱ ጉባኤዎችን የምታውጁባቸው የእግዚአብሔር በዓላት እነዚህ ናቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የእህሉንም ቁርባን፥ መሥዋዕቱንም፥ የመጠጡንም ቁርባን፥ ለጌታም በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን፥ እያንዳንዳቸውን ተገቢ በሆነው ቀናቸው እንድታቀርቡባቸው የተቀደሱ ጉባኤዎች እንዲሆኑ የምታውጁአቸው የጌታ በዓላት እነዚህ ናቸው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን፥ መሥ​ዋ​ዕ​ቱ​ንም፥ የመ​ጠ​ጡ​ንም ቍር​ባን፥ በየ​ቀኑ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቀ​ር​ቡ​ባ​ቸው ዘንድ የተ​ቀ​ደሱ በዓ​ላት እን​ዲ​ሆኑ የም​ታ​ው​ጁ​አ​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ላት እነ​ዚህ ናቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የእህሉንም ቍርባን፥ መሥዋዕቱንም፥ የመጠጡንም ቍርባን፥ በየቀኑ የእሳት ቍርባን ወደ እግዚአብሔር ታቀርቡባቸው ዘንድ የተቀደሱ ጉባኤዎች እንዲሆኑ የምታውጁአቸው የእግዚአብሔር በዓላት እነዚህ ናቸው።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 23:37
6 Referencias Cruzadas  

በዚህ ዓለም ለሚፈጸም ለማናቸውም ነገር ሁሉ እግዚአብሔር የወሰነለት ዘመንና ጊዜ አለው፤


“ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ የተቀደሱ ብላችሁ የምታውጁአቸው የእኔ የእግዚአብሔር በዓላት እነዚህ ናቸው፤


እነዚህም በዓላት ከእግዚአብሔር ሰንበቶች ጋር ተጨማሪ ሆነው የሚከበሩ ናቸው፤ ለእግዚአብሔር ከምትሰጡት ስጦታ ስእለት ሲፈጸምላችሁ ከምትሰጡት ስጦታና በፈቃዳችሁ ከምታቀርቡት ሁሉ ጋር ተደምረው የሚቀርቡ ናቸው።


ለእያንዳንዳቸው በተወሰነላቸው ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት እየተሰበሰባችሁ የምታከብሩአቸው ዋና ዋናዎቹ በዓላት እነዚህ ናቸው።


በዚህም ዐይነት ሙሴ እግዚአብሔርን ለማክበር ስለሚጠብቁአቸው የሃይማኖት በዓላት ይህን መመሪያ ለእስራኤል ሕዝብ ሰጠ።