“በአንተና በዘርህ፥ በመጪውም ትውልድ መካከል ቃል ኪዳኔን ለዘለዓለም አጸናለሁ፤ በዚህም ዐይነት ለአንተና ከአንተ በኋላ ለሚመጣው ዘርህ አምላክ እሆናለሁ።
ዘሌዋውያን 23:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ቀን የአምልኮ ስብሰባ እንዲሆንላችሁ ታውጃላችሁ፤ ምንም ሥራ አትሥሩ፤ ይህ በምትኖሩበት አገር ሁሉ ለልጅ ልጆቻችሁ የዘለዓለም ሥርዓት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ዕለት የተቀደሰ ጉባኤ ዐውጁ፤ የተለመደ ተግባራችሁንም አታከናውኑ፤ ይህም በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ለሚመጡት ትውልዶች የዘላለም ሥርዐት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ቀን ታውጃላችሁ፤ የተቀደሰ ጉባኤም ታደርጋላችሁ። የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት። በምትቀመጡበት አገር ሁሉ ለልጅ ልጃችሁ የዘለዓለም ሥርዓት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያችንም ቀን ቅድስት ጉባኤ ብላችሁ ታውጃላችሁ፤ የተግባር ሥራ ሁሉ አታድርጉባት፤ በምትቀመጡበት ሀገር ሁሉ ለልጅ ልጃችሁ የዘለዓለም ሥርዐት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሆንላችሁ ዘንድ ታውጃላችሁ፤ የተግባር ሥራ ሁሉ አታድርጉበት፤ በምትቀመጡበት አገር ሁሉ ለልጅ ልጃችሁ የዘላለም ሥርዓት ነው። |
“በአንተና በዘርህ፥ በመጪውም ትውልድ መካከል ቃል ኪዳኔን ለዘለዓለም አጸናለሁ፤ በዚህም ዐይነት ለአንተና ከአንተ በኋላ ለሚመጣው ዘርህ አምላክ እሆናለሁ።
አሮንና ልጆቹ ከምሽት እስከ ንጋት ይበራ ዘንድ የእግዚአብሔር መገኛ ከሆነው ፊት ከቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ካለው መጋረጃ ውጪ ያኑሩት፤ ይህም በእስራኤል ሕዝብና ወደፊትም በሚነሣው ትውልድ ዘንድ ቋሚ ሥርዓት ሆኖ ይኑር።
ይህንንም ስጦታ ለእግዚአብሔር ከማቅረባችሁ በፊት ከአዲሱ እህል ጥሬውን ወይም የተቈላውን ወይም እንጀራ ጋግራችሁ አትብሉ። ይህም ድንጋጌ በሚመጡት ዘመናት ሁሉ በልጅ ልጆቻችሁ ተጠብቆ ይኑር።
ካህኑም ከበኲራቱ እንጀራ ከሁለቱ ጠቦቶች ጋር በመወዝወዝ ለእግዚአብሔር ልዩ መባ አድርጎ ያቀርባል፤ እርሱም የካህናቱ ድርሻ ሆኖ ይነሣል፤ እነዚህም ስጦታዎች የተቀደሱ ናቸው።
ከእስራኤላውያን ወገን ስብ የሆነውን ሥጋ ወይም የእንስሶችን ደም የሚመገብ አይኑር፤ ይህም እስራኤላውያን በሚኖሩበት ዘመንና ቦታ ሁሉ ለዘለዓለሙ ተጠብቆ የሚኖር ቋሚ ሥርዓት ይሁን።
ከእንግዲህ ወዲህ ለመገናኛው ድንኳን እንክብካቤ የሚያደርጉትና ለእርሱም ሙሉ ኀላፊነት የሚኖራቸው ሌዋውያን ብቻ ናቸው፤ ይህም ለዘሮቻችሁ የሚተላለፍ የማይሻር ሕግ ሆኖ ይኖራል፤ ሌዋውያን ዘላቂነት ያለው ቋሚ ርስት በእስራኤል ምድር አይኖራቸውም።
ከወንዶችና ከሴቶች ልጆችህ፥ ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮችህ በከተሞችህ ከሚኖሩት ሌዋውያን፥ በአገርህ የሚኖሩ መጻተኞች፥ እናትና አባት ከሌላቸው ድኻ አደጎችና ባሎቻቸው ከሞቱባቸው ሴቶች ጋር በእግዚአብሔር ፊት እርሱ ለስሙ መጠሪያ እንዲሆን በመረጠው ቦታ በአንድነት ተሰብስበህ ደስ ይበልህ።