ዘሌዋውያን 14:50 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከወፎቹ አንዱን ንጹሕ የምንጭ ውሃ ባለበት የሸክላ ዕቃ ላይ ይረደው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከወፎቹም አንዱን በሸክላ ዕቃ ውስጥ ባለ የምንጭ ውሃ ላይ ይረድ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንደኛውንም ወፍ በሸክላ ዕቃ ውስጥ በምንጭ ውኃ ላይ ያርዳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንደኛዪቱንም ዶሮ በሸክላ ዕቃ ውስጥ ከምንጩ ውኃ በላይ ያርዳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንደኛውንም ወፍ በሸክላ ዕቃ ውስጥ ከምንጩ ውኃ በላይ ያርዳል። |
ከዚያም በኋላ የሊባኖሱን ዛፍ እንጨት፥ የሂሶጱን ቅጠል፥ የቀዩን ከፈይ ክርና በሕይወት ያለውን ወፍ በታረደው ወፍ ደምና በምንጩ ውሃ ውስጥ ይንከረው፤ ቤቱንም ሰባት ጊዜ ይርጨው።
ሌላውንም ወፍ ወስዶ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ቊራጭ፥ ከቀዩ ከፈይ ክርና ከሂሶጱ ቅጠል ጋር በአንድነት ቀድሞ በታረደው ወፍ ደም ውስጥ ይንከረው፤