ኤልሳዕም አንዱን አገልጋይ “ ‘ሄደህ በዮርዳኖስ ወንዝ ሰባት ጊዜ በመነከር ታጠብ፤ ከበሽታህም ፈጽሞ ትነጻለህ’ ብለህ ለዚህ ሰው ንገረው” ሲል አዘዘው፤
ዘሌዋውያን 13:58 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልብሱ በሚታጠብበት ጊዜ የሻጋታው ምልክት ቢጠፋ እንደገና ይጠበው፤ ከዚያም በኋላ የነጻ ይሆናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታጥቦ ከደዌ የጠራ ልብስ ወይም በሸማኔ ዕቃ የተሠራ ወይም በእጅ የተጠለፈ ጨርቅ ወይም ከቈዳ የተሠራ ማንኛውም ዕቃ እንደ ገና ይታጠብ፤ ንጹሕም ይሆናል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን አንተ ካጠብኸው ልብስ ወይም ከድሩ ወይም ከማጉ ወይም ከተለፋው ቆዳ ከተሠራ ከማናቸውም ነገር ላይ ደዌው ቢጠፋ፥ ሁለተኛ ጊዜ ይታጠባል፥ ንጹሕም ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልብሱ ወይም ድሩ ወይም ማጉ ወይም ከቆዳ የተደረገው ነገር ከታጠበ በኋላ ደዌው ቢለቅቀው ሁለተኛ ጊዜ ይታጠባል፤ ንጹሕም ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም ካጠብኸው ልብስ ወይም ከድሩ ወይም ከማጉ ወይም ከአጐዛው ከተደረገው ነገር ላይ ደዌው ቢጠፋ፥ ሁለተኛ ጊዜ ይታጠባል፥ ንጹሕም ይሆናል። |
ኤልሳዕም አንዱን አገልጋይ “ ‘ሄደህ በዮርዳኖስ ወንዝ ሰባት ጊዜ በመነከር ታጠብ፤ ከበሽታህም ፈጽሞ ትነጻለህ’ ብለህ ለዚህ ሰው ንገረው” ሲል አዘዘው፤
ስለዚህም ንዕማን የእግዚአብሔር ሰው ባዘዘው መሠረት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ወርዶ ሰባት ጊዜ በመነከር ታጠበ፤ ከበሽታውም ፈጽሞ ነጻ፤ ሥጋውም እንደ ትንሽ ልጅ ገላ በመታደስ ፍጹም ጤናማ ሆነ፤
ይህ እንግዲህ ከበፍታም ሆነ ከበግ ጠጒር፥ ወይም ከቈዳ በተሠራ ልብስ ላይ በድሩም ሆነ በማጉ በሻጋታ አማካይነት የሚተላለፍ ምልክት ተመርምሮ የሚታወቅበት የሥርዓት መመሪያ ነው።
እንግዲህ ወዳጆቼ ሆይ፥ ይህ ሁሉ ተስፋ የተሰጠው ለእኛ ስለ ሆነ ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ከማናቸውም ነገር ራሳችንን እናንጻ፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት ቅድስናችን ፍጹም እንዲሆን እናድርግ።
እነዚህ ነገሮች የመታደስ ጊዜ እስኪመጣ ድረስ በሥራ ላይ የዋሉ አፍአዊ ሥርዓቶች ናቸው፤ እነርሱ ስለ መብልና ስለ መጠጥ፥ ስለ ልዩ ልዩ የመንጻት ሥርዓቶችም ብቻ የተደረጉ ናቸው።