ተቀምጠውም ሆነ ቆመው በቅኔ በእኔ ላይ በአሽሙር የሚሳለቁ መሆናቸውን ተመልከት።
ተመልከታቸው! ቆመውም ሆነ ተቀምጠው፣ በዘፈናቸው ይሣለቁብኛል።
መቀመጣቸውንና መነሣታቸውን ተመልከት፥ እኔ መሳለቂያቸው ነኝ።
መቀመጣቸውንና መነሣታቸውን ተመልከት፤ እኔ መዝፈኛቸው ነኝ።
“አሁን ልጆቻቸው በዘፈን ያፌዙብኛል፤ በመካከላቸውም የመሳለቂያ ርእስ ሆኛለሁ።
አንተ ስቀመጥም ሆነ ስነሣ ታውቃለህ፤ ሐሳቤን ሁሉ ከሩቅ ሆነህ ታስተውላለህ።
እግዚአብሔር ሆይ! እኔ ግን ወደ አንተ እጸልያለሁ፤ አንተ በመረጥከው ጊዜ ጸሎቴን መልሰህ፥ በዘለዓለማዊው ፍቅርህ ማዳንህን አረጋግጥልኝ።
ለሕዝቤ ሁሉ መሳቂያ ሆንኩ፤ በዘፈናቸውም ቀኑን ሙሉ አፌዙብኝ።