ሰቈቃወ 3:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም የሚሆነው እርሱ በራሱ ፍላጎት በሰው ላይ ችግርንና ሐዘንን ስለማያመጣ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሆነ ብሎ ችግርን፣ ወይም መከራን በሰው ልጆች ላይ አያመጣምና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰውን ልጆች ከልቡ አያስጨንቅም፥ አያሳዝንምም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከልቡ አልተቈጣምና፥ የሰውንም ልጆች አላሳዘነምና፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰውን ልጆች ከልቡ አያስጨንቅም፥ አያሳዝንምም። |
እግዚአብሔር በጰራጺም ተራራ ላይና በገባዖን ሸለቆ ላይ እንዳደረገው፥ አሁንም ያልተለመደ ሥራውን ለመሥራትና ለሰው እንግዳ የሆነው ተግባሩን ለመፈጸም ይነሣል።
እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ ኃጢአተኛ ሰው፥ ኃጢአት መሥራቱን ትቶ በሕይወት እንዲኖር እንጂ በኃጢአቱ እንዲሞት አልፈቅድም፤ ስለዚህ እስራኤል ሆይ! ክፉ ሥራችሁን ተዉ፤ መሞትን ለምን ትፈልጋላችሁ? ብለህ ንገራቸው።