መሳፍንት 9:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአታም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ወደ ገሪዛን ተራራ ጫፍ ላይ ወጥቶ እንዲህ በማለት ወደ እነርሱ ጮኸ፤ “እናንተ የሴኬም ሰዎች! እኔን ብታዳምጡኝ እግዚአብሔርም እናንተን ያዳምጣችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአታም ይህ በተነገረው ጊዜ፣ በገሪዛን ተራራ ጫፍ ላይ ወጥቶ ድምፁን ከፍ በማድረግ እንዲህ አላቸው፤ “የሴኬም ገዦች ሆይ፤ እግዚአብሔር ይሰማችሁ ዘንድ እኔን ስሙኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአታም ይህ በተነገረው ጊዜ፥ በገሪዛን ተራራ ጫፍ ላይ ወጥቶ ድምጽን ከፍ በማድረግ እንዲህ አላቸው፤ የሴኬም ነዋሪዎች ሆይ፥ እግዚአብሔር ይሰማችሁ ዘንድ እኔን ስሙኝ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም ነገር ለኢዮአታም በነገሩት ጊዜ፥ ሄዶ በገሪዛን ተራራ ራስ ላይ ቆመ፤ ድምፁንም አንሥቶ አለቀሰ፤ እንዲህም አላቸው፥ “የሰቂማ ሰዎች ሆይ! ስሙኝ እግዚአብሔርም ይስማችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንም ነገር ለኢዮአታም በነገሩት ጊዜ፥ ሄዶ በገሪዛን ተራራ ራስ ላይ ቆመ፥ ድምፁንም እንሥቶ ጮኸ፥ እንዲህም አላቸው፦ የሴኬም ሰዎች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲሰማችሁ ስሙኝ። |
“እጆቻችሁን ወደ እኔ ለጸሎት ብትዘረጉ፥ ወደ እናንተ አልመለከትም፤ እጆቻችሁ በደም የተበከሉ ስለ ሆኑ የቱንም ያኽል ልመና ብታበዙ አልሰማችሁም፤
እነዚህም ተራራዎች ከዮርዳኖስ ማዶ በስተምዕራብ በኩል፥ በአራባ በሚኖሩት በከነዓናውያንም ምድር በጌልገላ ፊት ለፊት ከሞሬ ዛፍ አጠገብ የሚገኙ ናቸው።
“ዮርዳኖስን ከተሻገራችሁ በኋላ ሕዝቡን ለመባረክ በገሪዛን ተራራ ላይ መቆም የሚገባቸው የስምዖን፥ የሌዊ፥ የይሁዳ፥ የይሳኮር፥ የዮሴፍና የብንያም ነገዶች ናቸው።
የእስራኤልን ሕዝብ እንዲባርኩ ቀደም ብሎ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ባዘዘው መሠረት እስራኤላውያን ሁሉና መጻተኞች ሽማግሌዎቻቸው፥ ሹሞቻቸውና ዳኞቻቸው የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ከተሸከሙት ከሌዋውያን ካህናት ፊት ለፊት ግራና ቀኝ እኩሌቶቹ ከጌሪዚም ተራራ ፊት ለፊት፥ እኩሌቶቹ ደግሞ ከኤባል ተራራ ፊት ለፊት ቆሙ።
ከዚያን በኋላ የሴኬምና የቤትሚሎ ሕዝብ በአንድነት ተሰብስበው፥ በሴኬም ወደሚገኘው ወደተቀደሰው ወርካ ዛፍ ሄዱ፤ በዚያም አቤሜሌክን አነገሡ።