በሚወድቅበት ጊዜ እንደሚሞት ዐውቅ ስለ ነበር ወደ እርሱ ቀርቤ ገደልኩት፤ ከዚህ በኋላ ዘውዱን ከራሱ ላይ፥ አንባሩንም ከክንዱ ላይ ወሰድኩ፤ ጌታዬ ሆይ! እነሆ፥ እነርሱን ለአንተ አመጣሁልህ።”
መሳፍንት 9:54 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም የጦር መሣሪያ አንጋቹን ወጣት በፍጥነት በመጥራት፥ “ሰይፍህን መዘህ ግደለኝ፤ ሴት ገደለችው እንድባል አልፈልግም” ሲል አዘዘው። ስለዚህ ወጣቱ በሰይፍ መትቶ ገደለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወዲያውም ጋሻ ጃግሬውን ጠርቶ፣ “ ‘ሴት ገደለችው’ እንዳይሉ እባክህ ሰይፍህን መዝዘህ ግደለኝ” አለው። ስለዚህ አገልጋዩ ወጋው፤ እርሱም ሞተ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወዲያውም ጋሻ ጃግሬውን ጠርቶ፥ “‘ሴት ገደለችው’ እንዳይሉ እባክህ ሰይፍህን መዘህ ግደለኝ” አለው። ስለዚህ አገልጋዩ ወጋው፤ እርሱም ሞተ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ፈጥኖ ጋሻ ዣግሬውን ጠርቶ፥ “ሴት ገደለችው እንዳይሉ ሰይፍህን መዝዘህ ግደለኝ” አለው፤ ጐልማሳውም ወጋው፤ አቤሜሌክም ሞተ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ፈጥኖ ጋሻ ዣግሬውን ጠርቶ፦ እኔን፦ ሴት ገደለችው እንዳይሉ ሰይፍህን መዝዘህ ግደለኝ አለው፥ ጉልማሳውም ወጋው፥ ሞተም። |
በሚወድቅበት ጊዜ እንደሚሞት ዐውቅ ስለ ነበር ወደ እርሱ ቀርቤ ገደልኩት፤ ከዚህ በኋላ ዘውዱን ከራሱ ላይ፥ አንባሩንም ከክንዱ ላይ ወሰድኩ፤ ጌታዬ ሆይ! እነሆ፥ እነርሱን ለአንተ አመጣሁልህ።”
እርሱም በዚህ ጊዜ ወጣት ጋሻ ጃግሬውን “እነዚህ አረማውያን መሳለቂያ እንዳያደርጉኝ ሰይፍህን መዘህ ግደለኝ” አለው፤ ወጣቱ ግን ይህን ለማድረግ እጅግ ስለ ፈራ አላደረገውም፤ ስለዚህም ሳኦል የራሱን ሰይፍ መዞ በመሬት ላይ በመትከል በላዩ ላይ ወደቀ፤
እርስዋም “እሺ፥ እኔም ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሲሣራን ለሴት አሳልፎ ስለሚሰጥ ድሉ ለአንተ ክብር አይሆንም” አለችው፤ ስለዚህ ዲቦራ ከባራቅ ጋር ወደ ቃዴስ ዘመተች።
ከዚህ በኋላ ፍልስጥኤማውያን ዮናታንንና ጋሻጃግሬውን ጠርተው “የምንነግራችሁ ጉዳይ ስላለን ወደዚህ እኛ ወዳለንበት ኑ!” አሉአቸው። ዮናታንም ጋሻጃግሬውን “እንግዲህ ተከተለኝ፤ እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ላይ ድልን ለእስራኤል ይሰጣል” አለው፤
ዮናታንም በእጁና በጒልበቱ እየዳኸ ወደ አፋፉ ወጣ፤ ጋሻጃግሬውም ተከተለው፤ ዮናታንም በፍልስጥኤማውያን ላይ ድንገተኛ አደጋ በመጣል መታቸው፤ ጋሻጃግሬውም ገደላቸው።
ስለዚህም ሳኦል “እስቲ ወታደሮችን ቊጠሩና ከእኛ መካከል የጐደሉ እንዳሉ አረጋግጡ” ብሎ አዘዘ፤ በትእዛዙም መሠረት ሠራዊቱን በቈጠሩ ጊዜ ዮናታንና ጋሻጃግሬው አለመኖራቸው ታወቀ።