ከዚያም በኋላ ዳዊት ቤተሰቡን ሰላም ለማለት ወደ ቤት ገባ፤ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ልትቀበለው ወጣችና “የእስራኤል ንጉሥ ዛሬ ትልቅ ስም አግኝቶአል! በመኳንንቱ ገረዶች ፊት እንደ ቅሌታም ሽማግሌ እርቃኑን ገልጦአል!” አለችው።
መሳፍንት 9:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከባዓልበሪት ቤት ሰባ ጥሬ ብር ወስደው ሰጡት፤ አቤሜሌክም በዚያ በሰባ ጥሬ ብር ዋልጌዎችንና ወሮበሎችን ቀጥሮ እንዲከተሉት አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም በኣልብሪት ቤተ ጣዖት ሰባ ሰቅል ብር ሰጡት፤ አቢሜሌክም በዚያ ወሮበሎችንና ምናምንቴዎችን ቀጠረበት፤ እነርሱም ተከተሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም በኣልብሪት ቤተ ጣዖት ሰባ ሰቅል ናስ ሰጡት፤ አቤሜሌክም በዚያ ወሮበሎችንና ምናምንቴዎችን ቀጠረበት፤ እነርሱም ተከተሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከበዓልም ቤት ሰባ ብር ሰጡት፤ በዚያም አቤሜሌክ ወንበዴዎችንና አስደንጋጮችን ቀጠረበት፤ እነርሱም ተከትለውት ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከበኣልብሪትም ቤት ሰባ ብር ሰጡት፥ በዚያም አቤሜሌክ ምናምንቴዎችንና ወሮበሎችን ቀጠረበት፥ እነርሱም ተከተሉት። |
ከዚያም በኋላ ዳዊት ቤተሰቡን ሰላም ለማለት ወደ ቤት ገባ፤ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ልትቀበለው ወጣችና “የእስራኤል ንጉሥ ዛሬ ትልቅ ስም አግኝቶአል! በመኳንንቱ ገረዶች ፊት እንደ ቅሌታም ሽማግሌ እርቃኑን ገልጦአል!” አለችው።
ዘግየት ብሎም ኢዮርብዓም የማይረቡ ወሮበሎችን ሰበሰበ፤ እነርሱም በዕድሜው ማነስና በዕውቀት ያልበሰለ በመሆኑ ሊቋቋማቸው የማይችለውን የሰሎሞንን ልጅ ሮብዓምን በረቱበት።
አይሁድ ግን ቀንተው የሚበጠብጡ ሥራ ፈቶችን ከየመንገዱ ሰበሰቡና አሳደሙ። በከተማው ውስጥ ብጥብጥ እንዲነሣ አደረጉ፤ ጳውሎስንና ሲላስን አውጥተው ለሕዝቡ ለመስጠትም የኢያሶንን ቤት ከበቡ።
ጌዴዎን ከሞተ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ እንደገና ለእግዚአብሔር ያላቸውን ታማኝነት አጓድለው በዓሊም የተባሉትን ባዕዳን አማልክት አመለኩ፤ ለባዓልበሪትም ሰገዱ።
ሁሉም ወደ ወይን ተክሎቻቸው ወጥተው የወይን ፍሬ ለቀሙ፤ የወይን ጠጅ ጠምቀው ትልቅ በዓል አደረጉ፤ ወደ አምላካቸውም መቅደስ ገብተው በዚያ እየበሉና እየጠጡ ስለ አቤሜሌክ በማፌዝ ተናገሩ።
የተጨነቁ፥ ዕዳ ያለባቸው፥ እንዲሁም ሆድ የባሳቸው አንዳንድ ሰዎች ወደ እርሱ ስለ ሄዱ ብዛታቸው በድምሩ እስከ አራት መቶ ደረሰ፤ ዳዊትም የእነርሱ መሪ ሆነ።