ሑሻምም በሞተ ጊዜ የምድያምን ሰዎች በሞአብ ሜዳ ድል የመታው የበዳድ ልጅ ሀዳድ በእርሱ ተተክቶ ነገሠ፤ የነገሠባትም ከተማ ዐዊት ትባል ነበር።
መሳፍንት 7:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የንፍታሌም፥ የአሴርና መላው የምናሴ ነገድ ተጠርተው ወጥተው ምድያማውያንን አሳደዱ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በንፍታሌም፣ በአሴርና በመላው የምናሴ ምድር የሚገኙ እስራኤላውያን ተጠርተው ወጡ፤ ምድያማውያንንም አሳደዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በንፍታሌም፥ በአሴርና በመላው የምናሴ ምድር የሚገኙ እስራኤላውያን ተጠርተው ወጡ፤ ምድያማውያንንም አሳደዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ሰዎች ከንፍታሌምና ከአሴር፥ ከምናሴም ሁሉ ተሰብስበው ምድያምን አሳደዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ሰዎች ከንፍታሌምና ከአሴር ከምናሴም ሁሉ ተሰብስበው ምድያምን አሳደዱ። |
ሑሻምም በሞተ ጊዜ የምድያምን ሰዎች በሞአብ ሜዳ ድል የመታው የበዳድ ልጅ ሀዳድ በእርሱ ተተክቶ ነገሠ፤ የነገሠባትም ከተማ ዐዊት ትባል ነበር።
እያንዳንዱም ውጊያ የገጠመውን ጠላቱን ገደለ፤ ሶርያውያን ሸሹ፤ እስራኤላውያንም ያሳድዱአቸው ጀመር፤ ቤንሀዳድ ግን በፈረሱ ላይ በመቀመጥ ከጥቂት ፈረሰኞች ጋር ሸሽቶ አመለጠ፤
የምናሴን ነገድ ሁሉ መልእክት ልኮ ይከተሉት ዘንድ አስጠራቸው፤ እንዲሁም ወደ አሴር፥ ወደ ዛብሎንና ወደ ንፍታሌም ነገዶች መልእክተኞች ላከ፤ እነርሱም ከሌሎቹ ጋር ለመሰለፍ ወጡ።