እስራኤላውያንም ተጠርተው ከሚያስፈልጋቸው ስንቅና ትጥቅ ጋር ለጦርነት ተዘጋጁ፤ እነርሱም ወደ ጦርነቱ በመዝመት በሁለት ቡድን ተከፍለው ከሶርያውያን ፊት ለፊት ባለው ቦታ ሰፈሩ፤ የእስራኤል ወታደሮች ቊጥር አገሩን ካጥለቀለቀው ከሶርያውያን ሠራዊት ብዛት ጋር ሲነጻጸር ከሁለት የተከፈሉ የጥቂት ፍየሎች መንጋዎች ይመስሉ ነበር።
መሳፍንት 7:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዛታቸው እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ምድያማውያን፥ ዐማሌቃውያንና የምሥራቅ ሰዎች በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፤ ግመሎቻቸውም ከብዛታቸው የተነሣ እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ሊቈጠር የማይቻል ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብዛታቸው እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ምድያማውያን፣ አማሌቃውያንና ሌሎችም የምሥራቅ ሕዝቦች በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፤ የግመሎቻቸውም ብዛት በባሕር ዳርቻ እንዳለ አሸዋ ስፍር ቍጥር አልነበረውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብዛታቸው እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ምድያማውያን፥ አማሌቃውያንና ሌሎችም የምሥራቅ ሕዝቦች በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፤ የግመሎቻቸውም ብዛት በባሕር ዳርቻ እንዳለ አሸዋ ስፍር ቍጥር አልነበረውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዛታቸውም እንደ አንበጣ የሆነ ምድያማውያንና አማሌቃውያን የምሥራቅም ልጆች ሁሉ በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፤ የግመሎቻቸውም ብዛት ቍጥር እንደሌለው በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብዛታቸውም እንደ አንበጣ የሆነ ምድያማውያንና አማሌቃውያን የምሥራቅም ሰዎች ሁሉ በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፥ የግመሎቻቸውም ብዛት ቁጥር እንደሌለው በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ነበረ። |
እስራኤላውያንም ተጠርተው ከሚያስፈልጋቸው ስንቅና ትጥቅ ጋር ለጦርነት ተዘጋጁ፤ እነርሱም ወደ ጦርነቱ በመዝመት በሁለት ቡድን ተከፍለው ከሶርያውያን ፊት ለፊት ባለው ቦታ ሰፈሩ፤ የእስራኤል ወታደሮች ቊጥር አገሩን ካጥለቀለቀው ከሶርያውያን ሠራዊት ብዛት ጋር ሲነጻጸር ከሁለት የተከፈሉ የጥቂት ፍየሎች መንጋዎች ይመስሉ ነበር።
ከከብቶቻቸውና ከድንኳኖቻቸው ጋር ሲመጡ ያንበጣ መንጋ ይመስሉ ነበር፤ እነርሱንና ግመሎቻቸውን ለመቊጠር እስከማይቻል ድረስ እጅግ ብዙዎች ነበሩ፤ መጥተውም ምድሪቱን ያጠፉ ነበር።
ጌዴዎን እዚያ በደረሰ ጊዜ አንድ ሰው ያየውን ሕልም ለጓደኛው ሲነግረው ሰማ፤ ሕልሙም እንዲህ የሚል ነበር፦ “አንዲት የገብስ ቂጣ ከላይ ተንከባልላ ወርዳ ወደ ምድያም ሰፈር ደርሳ በዚያ ያለውን ድንኳን መታችው፤ ድንኳኑም ተገልብጦ በምድር ላይ ተዘረጋ።”
ዜባሕና ጻልሙናዕ ከምሥራቅ ሠራዊት ከተረፉት ዐሥራ አምስት ሺህ ወታደሮቻቸው ጋር በቃርቆር ነበሩ፤ አንድ መቶ ኻያ ሺህ መሣሪያ የታጠቁ ወንዶች አልቀው ነበር።
ፍልስጥኤማውያንም እስራኤላውያንን ለመውጋት ተሰበሰቡ፤ እነርሱም ከሠላሳ ሺህ የጦር ሠረገሎችና ከስድስት ሺህ ፈረሰኞች ጋር ብዛቱ እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የበዛ ሠራዊት ነበራቸው፤ ሄደውም በቤትአዌን በስተምሥራቅ ሚክማስ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ መሸጉ።
በምሽት ጊዜ ዳዊት በእነርሱ ላይ አደጋ ጥሎ እስከ ማግስቱ ማታ ድረስ ተዋጋቸው፤ በግመል ላይ ተቀምጠው እየጋለቡ ከሸሹት አራት መቶ ወጣቶች በስተቀር ከነዚያ ወራሪዎች ያመለጠ አንድም አልነበረም፤