እነርሱም የሚሉትን ትሰማለህ፤ ከዚያም በኋላ በእነርሱ ላይ አደጋ ለመጣል ድፍረት ታገኛለህ፤”። ስለዚህ ጌዴዎንና አገልጋዩ ፑራ ወደ ጠላት ሰፈር ዳርቻ ወረዱ፤
መሳፍንት 7:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ በሰፈሩ ላይ አደጋ ለመጣል ከፈራህ ግን ፑራ ተብሎ ከሚጠራው አገልጋይህ ጋር ወደ ሰፈሩ ውረድ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አደጋ ለመጣል የምትፈራ ከሆነ ግን፣ ፉራ ከተባለው አገልጋይህ ጋራ ወደ ሰፈሩ ውረድ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አደጋ ለመጣል የምትፈራ ከሆነ ግን፥ ፉራ ከተባለው አገልጋይህ ጋር ወደ ሰፈሩ ውረድ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብቻህንም ለመውረድ ብትፈራ አንተ ከሎሌህ ፋራን ጋር ወደ ሰፈሩ ውረድ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም ለመውረድ ብትፈራ አንተ ከሎሌህ ከፉራ ጋር ወደ ሰፈሩ ውረድ፥ |
እነርሱም የሚሉትን ትሰማለህ፤ ከዚያም በኋላ በእነርሱ ላይ አደጋ ለመጣል ድፍረት ታገኛለህ፤”። ስለዚህ ጌዴዎንና አገልጋዩ ፑራ ወደ ጠላት ሰፈር ዳርቻ ወረዱ፤
በዚያም ሌሊት እግዚአብሔር ጌዴዎንን እንዲህ አለው፥ “በእነርሱ ላይ ድልን እንድትቀዳጅ የማደርግህ ስለ ሆነ ተነሥተህ የእነርሱን ሰፈር አጥቃ።
ከዚህም በኋላ ዳዊት ሒታዊውን አቤሜሌክንና ከጸሩያ ልጆች የኢዮአብን ወንድም አቢሳን “ከእናንተ ከሁለታችሁ ከእኔ ጋር አብሮ ወደ ሳኦል ሰፈር የሚሄድ ማን ነው?” ሲል ጠየቃቸው። አቢሻይም “እኔ እሄዳለሁ” ሲል መለሰ።