ይህንንም የማደርገው ሕዝቡ እኔን ስለ ተዉና ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት በማቅረብ ይህን ስፍራ ስላረከሱ ነው፤ እነርሱም ሆኑ የቀድሞ አባቶቻቸው ከይሁዳ ነገሥታት ጭምር ስለ ነዚህ አማልክት የሚያውቁት ነገር የለም፤ ይህ ብቻ ሳይሆን ንጹሖች ሰዎችን በመግደል ይህ ስፍራ በደም የተሞላ እንዲሆን አድርገውታል።
መሳፍንት 5:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን ቀድሞ የማያውቁአቸውን ባዕዳን አማልክትን በመረጡ ጊዜ፥ በምድሪቱ ላይ ጦርነት ሆነ፤ ከአርባ ሺህ እስራኤላውያን ጋሻና ጦር የያዘ አንድ ሰው እንኳ አልነበረም! አዲሱ መደበኛ ትርጒም አዳዲስ አማልክትን በተከተሉ ጊዜ፣ ጦርነት እስከ ከተማው በር መጣ፤ ጋሻም ሆነ ጦር፣ በአርባ ሺሕ እስራኤላውያን መካከል አልተገኘም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አዲሶች አማልክትን መረጡ፥ በዚያ ጊዜ ሰልፍ በበሮች ሆነ፥ በአርባ ሺህ በእስራኤል ዘንድ ጦርና ጋሻ አልታየም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አዲሶች አማልክትን መረጡ፤ በዚያ ጊዜ ሰልፍ በበሮች ሆነ፤ በአርባ ሺህ በእስራኤል ዘንድ ጦርና ጋሻ አልታዩም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አዲሶች አማልክትን መረጡ፥ በዚያ ጊዜ ሰልፍ በበሮች ሆነ፥ በአርባ ሺህ በእስራኤል ዘንድ ጦርና ጋሻ አልታየም። |
ይህንንም የማደርገው ሕዝቡ እኔን ስለ ተዉና ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት በማቅረብ ይህን ስፍራ ስላረከሱ ነው፤ እነርሱም ሆኑ የቀድሞ አባቶቻቸው ከይሁዳ ነገሥታት ጭምር ስለ ነዚህ አማልክት የሚያውቁት ነገር የለም፤ ይህ ብቻ ሳይሆን ንጹሖች ሰዎችን በመግደል ይህ ስፍራ በደም የተሞላ እንዲሆን አድርገውታል።
ከግብጽ ያወጣቸውን የቀድሞ አባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ማገልገል ተዉ፤ በዚህም ፈንታ በዙሪያቸው ያሉ ሕዝቦች የሚያመልኩአቸውን የውሸት አማልክትን ማገልገል ጀመሩ፤ ለእነርሱም በመስገድ እግዚአብሔርን አስቈጡት።
ነገር ግን የእስራኤል ሕዝብ ለመሪዎቻቸው የማይታዘዙ ሆኑ፤ ለእግዚአብሔርም ያላቸውን ታማኝነት አጓድለው የሌሎች ባዕዳን አማልክት አገልጋዮች ሆኑ፤ አባቶቻቸው የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ያከብሩ ነበር፤ እነርሱ ግን የአባቶቻቸውን ምሳሌ አልተከተሉም።
ያቢን ዘጠኝ መቶ የብረት ሠረገሎች ነበሩት፤ የእስራኤል ሕዝብ በጭካኔና በዐመፅ ለኻያ ዓመት ገዛቸው፤ ከዚያም በኋላ የእስራኤል ሕዝብ እንዲረዳቸው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።
እነሆ አድምጡ! ውሃ በሚቀዳባቸው ጒድጓዶች ዙሪያ የሚሰማው የብዙ ሰዎች ድምፅ፥ የእግዚአብሔርን ድል ያበሥራል፤ የእስራኤልንም ሕዝብ ድል አድራጊነት ይናገራል። ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ሕዝብ፥ ከከተሞቻቸው ተሰልፈው ወረዱ።