መሳፍንት 5:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለምን በበጎች መካከል ዘገየህ? ለበጎች የሚደረገውን ፉጨት ለመስማት ነውን? ለመምጣት ወይም ላለመምጣት አመነታ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በበጎች ጕረኖ መካከል ለምን ተቀመጥህ? መንጎችን የሚጠራውን ፉጨት ለመስማት ነውን? በሮቤል አውራጃዎች፣ ብዙ የልብ ምርምር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንጎች ሲያፍዋጩ ለመስማት በበጎች ጉረኖ መካከል ለምን ተቀመጥህ? በሮቤል ፈሳሾች አጠገብ ታላቅ የልብ ምርምር ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንጎች ሲያፍዋጩ ለመስማት፥ በበጎች ጉረኖ መካከል ለምን ተቀመጥህ? በሮቤል ፈሳሾች አጠገብ ታላቅ የልብ ምርምር ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንጎች ሲያፍዋጩ ለመስማት በበጎች ጉረኖ መካከል ለምን ተቀመጥህ? በሮቤል ፈሳሾች አጠገብ ታላቅ የልብ ምርምር ነበረ። |
የእነርሱ አምላክ ሆዳቸው ነው፤ አሳፋሪ የሆነ ነገር ለእነርሱ ክብራቸው ነው፤ ሐሳባቸውም የሚያተኲረው በምድራዊ ነገር ላይ ነው፤ ስለዚህ የእነርሱ መጨረሻ ጥፋት ነው።
የይሳኮር መሪዎች ከዲቦራ ጋር መጡ፤ አዎ፥ ይሳኮርም ባራቅም መጡ፤ ወደ ሸለቆው ተከተሉት፤ ነገር ግን የሮቤል ነገድ ለሁለት ተከፈለ፤ ለመምጣት ወይም ላለመምጣት አመነታ።