ሒልቂያ፥ አሒቃም፥ ዐክቦር፥ ሳፋንና ዐሣያ በኢየሩሳሌም አዲስ በተሠራው ሰፈር የምትኖረውን ሑልዳ ተብላ የምትጠራውን ነቢይት ለመጠየቅ ሄዱ፤ የሐርሐስ የልጅ ልጅ የቲቅዋ ልጅ የሆነው ባልዋ ሻሉም የቤተ መቅደስ አልባሳት ኀላፊ ነበር፤ እነርሱም የሆነውን ሁሉ ለነቢይቱ አስረዱአት።
መሳፍንት 4:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ የላፒዶት ሚስት የሆነች “ዲቦራ” የምትባል ነቢይት ነበረች፤ እርስዋም በዚያን ጊዜ የእስራኤል መሪ ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ የለፊዶት ሚስት ነቢዪቱ ዲቦራ በእስራኤል ላይ ፈራጅ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ የለፊዶት ሚስት ነቢዪቱ ዲቦራ በእስራኤል ላይ ፈራጅ ነበረች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ወራት ነቢይቱ የለፊዶት ሚስት ዲቦራ እስራኤልን ትገዛቸው ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያ ጊዜም ነቢይቱ የለፊዶት ሚስት ዲቦራ በእስራኤል ላይ ትፈርድ ነበረች። |
ሒልቂያ፥ አሒቃም፥ ዐክቦር፥ ሳፋንና ዐሣያ በኢየሩሳሌም አዲስ በተሠራው ሰፈር የምትኖረውን ሑልዳ ተብላ የምትጠራውን ነቢይት ለመጠየቅ ሄዱ፤ የሐርሐስ የልጅ ልጅ የቲቅዋ ልጅ የሆነው ባልዋ ሻሉም የቤተ መቅደስ አልባሳት ኀላፊ ነበር፤ እነርሱም የሆነውን ሁሉ ለነቢይቱ አስረዱአት።
እኔም “አምላክ ሆይ፥ ጦቢያና ሰንባላጥ ያደረጉትን ሁሉ ተመልከት፤ ፍረድባቸውም፤ ኖዓድያ የተባለችው ሴት ነቢይትና ሌሎቹም ነቢያት እኔን ለማስፈራራት ያደረጉትን ሁሉ አስብ” በማለት ጸለይኩ።
እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “አሁንም የሰው ልጅ ሆይ! በሕዝብህ መካከል ከአሳባቸው አፍልቀው ትንቢት በሚናገሩት ሴቶች ላይ አተኲረህ ትንቢት ተናገርባቸው፤
እንዲሁም በዚያን ጊዜ ከአሴር ነገድ የሆነች የፋኑኤል ልጅ ሐና የምትባል አንዲት ነቢይት ነበረች። በዕድሜዋም በጣም የገፋች ሴት ነበረች፤ ከባልዋ ጋር ሰባት ዓመት ከተቀመጠች በኋላ ባልዋ ሞተባት፤
እንዲሁም ራስዋን ሳትከናነብ የምትጸልይ ወይም የትንቢት ቃል የምትናገር ሴት በሴት ላይ ሥልጣን ያለውን ወንድን ታዋርዳለች፤ ራስዋን የማትከናነብ ሴት እንደ ተላጨች ትቈጠራለች።
ያቢን ዘጠኝ መቶ የብረት ሠረገሎች ነበሩት፤ የእስራኤል ሕዝብ በጭካኔና በዐመፅ ለኻያ ዓመት ገዛቸው፤ ከዚያም በኋላ የእስራኤል ሕዝብ እንዲረዳቸው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።
ይህችም ነቢይት በተራራማው በኤፍሬም አገር በራማና በቤትኤል መካከል በሚገኘው የዲቦራ የተምር ዛፍ ሥር ተቀምጣ ትፈርድ ስለ ነበር የእስራኤል ሕዝብ ፍርድ ለማግኘት ወደ እርስዋ ይሄዱ ነበር።