መሳፍንት 4:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአቢኒዓም ልጅ ባራቅ ወደ ታቦር ተራራ መሄዱ ለሲሣራ ተነገረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአቢኒኤም ልጅ ባርቅ ወደ ታቦር ተራራ መሄዱን ሲሣራ በሰማ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአቢኒዔም ልጅ ባራቅ ወደ ታቦር ተራራ መሄዱን ሲሣራ በሰማ ጊዜ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአቢኒሔምም ልጅ ባርቅ ወደ ታቦር ተራራ እንደ ወጣ ለሲሣራ ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአቢኒኤምም ልጅ ባርቅ ወደ ታቦር ተራራ እንደ ወጣ ለሲሣራ ነገሩት። |
“ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር” ተብሎ የሚጠራው ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ “እኔ ሕያው ነኝ፤ በተራሮች መካከል ታቦር፥ በባሕር አጠገብ ቀርሜሎስ ከፍ ብለው እንደሚታዩ እንደዚሁ በእናንተ ላይ ከፍ ብሎ የሚታይ፥ ኀይል ይመጣል።
“ካህናት ሆይ! ይህን ስሙ! እናንተም የእስራኤል ሕዝብ አስተውሉ! እናንተም ንጉሣውያን ቤተሰብ ይህን አድምጡ! እነሆ ፍርድ በእናንተ ላይ መጥቶአል፤ በምጽጳ እንደ ወጥመድ፥ በታቦርም እንደ ተዘረጋ መረብ ሆናችኋል።
ድንበሩም መመለሻው የዮርዳኖስ ወንዝ ሆኖ፥ ከታቦር፥ ከሻሐጹማና ከቤትሼሜሽ ጋር ይዋሰናል፤ እርሱም ዐሥራ ስድስት ከተሞችንና በዙሪያቸው ያሉትን ታናናሽ ከተሞች ሁሉ ያጠቃልላል፤
ከዚህ በኋላ ድንበሩ በምዕራብ በኩል ወደ አዝኖትታቦር ይታጠፋል፤ ከዚያም ወደ ሁቆቅ ይሄዳል፤ በደቡብ በኩል ዛብሎን፥ በምዕራብ በኩል አሴርን፥ በስተምሥራቅ ዮርዳኖስ የሚያዋስነው ይሁዳን ነው።
ቀኔናዊው ሔቤር የሙሴ ዐማት ከነበረው ከሆባብ ልጆች ከቄናውያን ተለየ፤ ወደ ቃዴስ ቀረብ ብሎ በጸእናይም በሚገኘው በታላቁ ዛፍ አጠገብ ድንኳኑን ተከለ።
ሲሣራም ዘጠኝ መቶ የብረት ሠረገሎችንና ከእርሱ ጋር የነበረውን ሠራዊት ሁሉ የአሕዛብ ይዞታ ከነበረችው ከሐሮሼት ወደ ቂሶን ወንዝ ሰበሰበ።
የአቢኒዓምን ልጅ ባራቅን የንፍታሌም ድርሻ ከሆነችው ከቃዴስ ከተማ አስጠርታ እንዲህ አለችው፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይህን ትእዛዝ ሰጥቶሃል፦ ‘ከንፍታሌምና ከዛብሎን ነገዶች ዐሥር ሺህ ሰዎች መርጠህ ወደ ታቦር ተራራ ውሰዳቸው፤
ከዚህ በኋላ ጌዴዎን “በታቦር የገደላችኋቸው ሰዎች እንዴት ያሉ ነበሩ?” ሲል ዜባሕንና ጻልሙናዕን ጠየቀ። እነርሱም “አንተን ይመስሉ ነበር፤ እያንዳንዳቸው የንጉሥ ልጅ ይመስላሉ” አሉት።