ንጉሥ አክዓብ መልእክተኞቹን “ ‘እውነተኛ ወታደር መደንፋት የሚገባው ከጦርነት ድል በኋላ እንጂ ከጦርነት በፊት አይደለም’ ብላችሁ ለንጉሥ ቤንሀዳድ ንገሩት” ሲል መለሰላቸው።
መሳፍንት 4:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባራቅም የንፍታሌምንና የዛብሎንን ነገዶች ወደ ቃዴስ አስጠራ፤ ከእነርሱም ዐሥር ሺህ ሰዎች ተከተሉት፤ ዲቦራም አብራው ዘመተች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም ባርቅ የዛብሎንንና የንፍታሌምን ሰዎች ወደ ቃዴስ ጠራቸው፤ ዐሥር ሺሕ ሰዎች ተከተሉት፤ ዲቦራም ዐብራው ሄደች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባራቅ ለዛብሎንና ለንፍታሌም ሰዎች ጥሪ አስተላለፈ፤ ዐሥር ሺህ ሰዎች ተከተሉት፤ ዲቦራም አብራው ሄደች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባርቅም ዛብሎንንና ንፍታሌምን ወደ ቃዴስ ጠራቸው፤ ዐሥር ሺህም ሰዎች ተከትለውት ወጡ፤ ዲቦራም ከእርሱ ጋር ወጣች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባርቅም ዛብሎንንና ንፍታሌምን ወደ ቃዴስ ጠራቸው፥ አሥር ሺህም ሰዎች ተከትለውት ወጡ፥ ዲቦራም ከእርሱ ጋር ወጣች። |
ንጉሥ አክዓብ መልእክተኞቹን “ ‘እውነተኛ ወታደር መደንፋት የሚገባው ከጦርነት ድል በኋላ እንጂ ከጦርነት በፊት አይደለም’ ብላችሁ ለንጉሥ ቤንሀዳድ ንገሩት” ሲል መለሰላቸው።
ሙሴም “መኳንንትህ ሁሉ ወደ እኔ መጥተው እጅ ይነሡኛል፤ ሕዝቤንም ይዤ እንድወጣ ይለምኑኛል፤ ከዚያም በኋላ እሄዳለሁ” በማለት ንግግሩን አበቃ፤ ይህንንም ከተናገረ በኋላ በታላቅ ቊጣ ከንጉሡ ፊት ወጥቶ ሄደ።
ዲቦራም ባራቅን “እግዚአብሔር አንተን በሲሣራ ላይ ድልን እንድትቀዳጅ የሚያደርግበት ቀን ዛሬ ስለ ሆነ ተነሥ! እነሆ! እግዚአብሔር ይመራሃል” አለችው፤ ባራቅም ዐሥር ሺህ ወታደሮች ተከትለውት ከታቦር ተራራ ወረደ።
የአቢኒዓምን ልጅ ባራቅን የንፍታሌም ድርሻ ከሆነችው ከቃዴስ ከተማ አስጠርታ እንዲህ አለችው፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይህን ትእዛዝ ሰጥቶሃል፦ ‘ከንፍታሌምና ከዛብሎን ነገዶች ዐሥር ሺህ ሰዎች መርጠህ ወደ ታቦር ተራራ ውሰዳቸው፤
የይሳኮር መሪዎች ከዲቦራ ጋር መጡ፤ አዎ፥ ይሳኮርም ባራቅም መጡ፤ ወደ ሸለቆው ተከተሉት፤ ነገር ግን የሮቤል ነገድ ለሁለት ተከፈለ፤ ለመምጣት ወይም ላለመምጣት አመነታ።
የምናሴን ነገድ ሁሉ መልእክት ልኮ ይከተሉት ዘንድ አስጠራቸው፤ እንዲሁም ወደ አሴር፥ ወደ ዛብሎንና ወደ ንፍታሌም ነገዶች መልእክተኞች ላከ፤ እነርሱም ከሌሎቹ ጋር ለመሰለፍ ወጡ።