መሳፍንት 3:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤሁድ ግብሩን ለንጉሡ ካቀረበ በኋላ ግብሩን ተሸክመው የነበሩትን ሰዎች ወደ ቤታቸው ተመልሰው እንዲሄዱ አደረገ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ናዖድም ግብሩን ካቀረበ በኋላ፣ ግብር ተሸክመው የመጡት ሰዎች ተመልሰው እንዲሄዱ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤሁድ ግብሩን ካቀረበ በኋላ፥ ግብር ተሸክመው የመጡትን ሰዎች ተመልሰው እንዲሄዱ አደረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እጅ መንሻውንም ማቅረብ በጨረሰ ጊዜ፥ እጅ መንሻ የተሸከሙትን ሰዎች አሰናበታቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ግብሩንም ማቅረብ በጨረሰ ጊዜ፥ ግብር የተሸከሙትን ሰዎች ሰደደ። |
ኤሁድ ራሱ ግን በጌልገላ አጠገብ ወዳሉት ተጠርበው ወደ ተተከሉ የጣዖት ድንጋዮች ዞር ብሎ ቈየ፤ ወደ ዔግሎንም ተመልሶ “ንጉሥ ሆይ! በግል ለአንተ የምነግርህ አንድ ምሥጢር አለኝ” አለው። እርሱም “ዝም በል” አለው። ስለዚህም ንጉሡ ባለሟሎቹን “እስቲ አንድ ጊዜ ውጪ ቈዩልን!” አላቸው፥ እነርሱም በሙሉ ወጡ።