በገባዖን ወደሚገኘው ወደ ትልቁ ድንጋይ በደረሱ ጊዜ ዐማሣ አገኛቸው፤ በዚህን ጊዜ ኢዮአብ ሰይፉን በሰገባው ከቶ፥ ሰገባውንም በመታጠቂያው ላይ አስሮ ለጦርነት ተዘጋጅቶ ነበር፤ እየተራመደ ወደ ፊት ሲሄድ ሳለም ሰይፉ ወደቀ፤
መሳፍንት 3:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤሁድ ኀምሳ ሳንቲ ሜትር የሚያኽል ርዝመት ያለው በሁለት በኩል ስለ ታም የሆነ ሰይፍ ለራሱ አሠራ፤ እርሱንም በቀኝ ጭኑ በኩል በልብሱ ውስጥ ታጠቀው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም በሁለት በኩል ስለታም የሆነና አንድ ክንድ ተኩል ርዝመት ያለው ሰይፍ አዘጋጅቶ በልብሱ ውስጥ በቀኝ ጭኑ ላይ አሰረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም በሁለት በኩል ስለታም የሆነና አንድ ክንድ ተኩል ርዝመትተ ያለው ሰይፍ አዘጋጅቶ በልብሱ ውስጥ በቀኝ ጭኑ ላይ አሰረው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ናዖድም ሁለት አፍ ያላት ርዝመቷ አንድ ስንዝር የሆነች ሰይፍ አበጀ፤ ከልብሱም በታች በቀኝ በኩል በወገቡ ታጠቃት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ናዖድም ሁለት አፍ ያለው ርዝመቱ አንድ ክንድ የሆነ ሰይፍ አበጀ፥ ከልብሱም በታች በቀኝ ጭኑ በኩል አደረገው። |
በገባዖን ወደሚገኘው ወደ ትልቁ ድንጋይ በደረሱ ጊዜ ዐማሣ አገኛቸው፤ በዚህን ጊዜ ኢዮአብ ሰይፉን በሰገባው ከቶ፥ ሰገባውንም በመታጠቂያው ላይ አስሮ ለጦርነት ተዘጋጅቶ ነበር፤ እየተራመደ ወደ ፊት ሲሄድ ሳለም ሰይፉ ወደቀ፤
ሁሉም በሰይፍ አያያዝ የሠለጠኑና በጦርነትም የተፈተኑ ናቸው፤ በሌሊት ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ለመመከት እያንዳንዱ ሰይፉን እንደ ታጠቀ ያድራል።
የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና የሚሠራ ነው፤ ሁለት አፍ ካለው ሰይፍ ይልቅ ስለታም ነው፤ ነፍስንና መንፈስን፥ ጅማትንና ቅልጥምን እስኪለያይ ድረስ የሚቈራርጥ ነው፤ በልብ ውስጥ የተሰወረውንም ሐሳብና ምኞት መርምሮ የሚፈርድ ነው።
በቀኝ እጁ ሰባት ኮከቦችን ይዞ ነበር፤ በሁለት በኩል ስለት ያለው ሰይፍ ከአፉ ይወጣ ነበር፤ ፊቱም በሙሉ ድምቀቱ እንደሚያበራ ፀሐይ ነበረ።
ከዚህ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም ከብንያም ነገድ ግራኝ የነበረውን የጌራን ልጅ ኤሁድን አዳኝ አድርጎ አስነሣቸው፤ የእስራኤል ሕዝብ ኤሁድን ግብር አስይዘው ወደ ሞአብ ንጉሥ ወደ ዔግሎን ላኩት።