መሳፍንት 2:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያ ስፍራ “ቦኪም” ተብሎ የተጠራውም በዚህ ምክንያት ነው፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያን ስፍራ ቦኪም ብለው ጠሩት፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያንን ስፍራ ቦኪምሠ ብለው ጠሩት፤ በዚያም ለጌታ መሥዋዕት አቀረቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዚያም ስፍራ ስም “መካነ ብካይ” ተብሎ ተጠራ፤ በዚያም ለእግዚአብሔር ሠዉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዚያንም ስፍራ ስም ቦኪም ብለው ጠሩት፥ በዚያም ለእግዚአብሔር ሠዉ። |
በእርሱም ላይ እስከ ዛሬ ድረስ የሚታይ ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩበት፤ እግዚአብሔርም ከቊጣው ተመለሰ፤ ስለዚህም ያ ቦታ የአኮር ሸለቆ ተብሎ ይጠራል።
ከዚህ በኋላ ማኑሄ አንድ የፍየል ጠቦትና የእህል ቊርባን ወስዶ በአለቱ መሠዊያ ላይ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ ማኑሄና ሚስቱም እየተመለከቱ ሳለ እግዚአብሔር አስደናቂ ነገር አደረገ።
የእግዚአብሔር መልአክ ከጌልጌላ ወደ ቦኪም ሄዶ እስራኤላውያንን እንዲህ አላቸው፤ “እኔ ከግብጽ ምድር አውጥቼ ለቀድሞ አባቶቻችሁ ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር አመጣኋችሁ፤ እንዲህም አልኩ፦ ‘ከእናንተ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ከቶ አላፈርስም፤
ጌዴዎንም በዚያ መሠዊያ ሠርቶ “እግዚአብሔር የሰላም አምላክ ነው” ብሎ ሰየመው፤ (ይህም መሠዊያ እስከ ዛሬ የአቢዔዜር ጐሣ ይዞታ በሆነችው በዖፍራ ቆሞ ይገኛል።)
ሳሙኤልም ገና ጡት ያልተወ ትንሽ የበግ ጠቦት ዐርዶ በሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ ለእግዚአብሔር አቀረበው፤ ከዚህም በኋላ ስለ እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰማለት፤