መሳፍንት 2:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር መስፍን ባስነሣላቸው ጊዜ ሁሉ እርሱ ከመስፍኑ ጋር ነበር፤ በሚያሳድዱአቸውና በሚጨቊኑአቸው ጠላቶች ምክንያት ሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር በሚጮኹበት ጊዜ እግዚአብሔር ያዝንላቸው ስለ ነበረ በመስፍኑ ዘመን ሁሉ ከጠላቶቻቸው እጅ ያድናቸው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር መሳፍንትን ባሰነሣላቸው ቍጥር ከመስፍኑ ጋራ ስለሚሆን፣ እርሱ በሕይወት እስካለ ድረስ እግዚአብሔር ከጠላቶቻቸው ያድናቸው ነበር፤ ከጠላቶቻቸው ሥቃይና መከራ ሲደርስባቸው በሚጮኹበት ጊዜ እግዚአብሔር ይራራላቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ መሳፍንትን ባስነሣላቸው ጊዜ ከመስፍኑ ጋር ስለሚሆን፥ እርሱ በሕይወት እስካለ ድረስ ጌታ ከጠላቶቻቸው ያድናቸው ነበር፤ ከጠላቶቻቸው ሥቃይና መከራ ሲደርስባቸው በሚጮኹበት ጊዜ ጌታ ይራራላቸው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም መሳፍንትን ባስነሣላቸው ጊዜ እግዚአብሔር ከመስፍኑ ጋር ነበረ፤ እግዚአብሔርም በሚዋጉአቸው ሰዎች ፊት ከመከራቸው የተነሣ ይቅር ብሏቸዋልና በመስፍኑ ዘመን ሁሉ ከጠላቶቻቸው እጅ አዳናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም መሳፍንትን ባስነሣላቸው ጊዜ እግዚአብሔር ከመስፍኑ ጋር ነበረ፥ እግዚአብሔርም ስለሚጋፉአቸውና ስለሚያስጨንቋቸው በጩኸታቸው ያዝን ነበርና በመስፍኑ ዘመን ሁሉ ከጠላቶቻቸው እጅ አዳናቸው። |
ከዚህ በኋላ ኢዮአካዝ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የሶርያ ንጉሥ በእስራኤላውያን ላይ የፈጸመባቸው ግፍ እጅግ ከባድ መሆኑን ተመልክቶ የኢዮአካዝን ጸሎት ሰማ።
እግዚአብሔር ግን “ችግረኞች ተጨቊነዋል፤ ስደተኞች በመከራ ብዛት ይቃትታሉ፤ ስለዚህ እነርሱ የሚፈልጉትን ደኅንነት ለመስጠት እነሣለሁ” ይላል።
እግዚአብሔርም መልሶ “አይዞህ እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔ እንደ ላክኹህም ምልክት የሚሆንህ ይህ ነው፤ ሕዝቤን ከግብጽ በምታወጣበት ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እኔን ታመልኩኛላችሁ” አለው።
“እስራኤል ሆይ! እንዴት እተውሃለሁ? እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? በአዳማና በጸቦይም ያደረግኹትንስ፥ እንዴት አደርግብሃለሁ? ለአንተ ያለኝ ፍቅር ታላቅ ስለ ሆነ፥ ይህን ሁሉ ላደርግብህ አልፈቅድም!
እግዚአብሔር የነነዌ ሰዎች ያደረጉትንና ከክፉ መንገዳቸው መመለሳቸውን ተመለከተ፤ ስለዚህም ራርቶላቸው በእነርሱ ላይ ሊያመጣ የነበረውን ቅጣት አልፈጸመም።
“በአገራችሁ ላይ ጦርነት አንሥቶ አደጋ የጣለባችሁን ጠላት ለመከላከል ስትሄዱ በእኔ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ዘንድ እንድትታወሱ በመለከቶቻችሁ የማስጠንቀቂያ ድምፅ ንፉ፤ እኔ አምላካችሁም አድናችኋለሁ።
አንተ ኢያሱ፥ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ አንተን ተቋቊሞ ድል የሚነሣህ ማንም አይኖርም፤ እኔ ከሙሴ ጋር እንደ ነበርኩ ከአንተም ጋር እሆናለሁ፤ ሁልጊዜም ከአንተ ጋር ነኝ፤ ከቶም አልተውህም፤
ነገር ግን መሪ በሚሞትበት ጊዜ ሁሉ ተመልሰው ሌሎች አማልክትን በመከተል፥ ለእነርሱም በመስገድና እነርሱንም በማምለክ ከአባቶቻቸው የከፋ በደል ይፈጽሙ ነበር፤ መጥፎ ድርጊታቸውንና ልበ ደንዳና መሆናቸውን አልተዉም።
ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም የሚያድናቸውን አዳኝ የካሌብ ታናሽ ወንድም ልጅ የሆነውን የቄኔዝን ልጅ ዖትኒኤልን አስነሣቸው።