ስለዚህም ጠላቶቻቸው እነርሱን ድል አድርገው ይገዙአቸው ዘንድ አሳልፈህ ሰጠሃቸው፤ እነርሱም አስጨነቁአቸው። በችግራቸውም ጊዜ ወደ አንተ ጮኹ፤ አንተም በሰማይ ሆነህ ሰማሃቸው፤ ከምሕረትህ ታላቅነት የተነሣ፥ ከጠላቶቻቸው የሚታደጉ መሪዎችን ላክህላቸው።
መሳፍንት 2:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ከወራሪዎቻቸው እጅ የሚያድኑአቸውን መሳፍንት ተብለው የሚጠሩ መሪዎችን አስነሣላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም ከእነዚህ ወራሪዎች የሚያድኗቸውን መሳፍንት አስነሣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ከእነዚህ ወራሪዎች እጅ የሚያድኗቸውን መሳፍንት አስነሣላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም መሳፍንትን አስነሣላቸው፤ ከሚማርኳቸውም እጅ አዳኗቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም መሳፍንትን አስነሣላቸው፥ ከሚማርኩአቸውም እጅ አዳኑአቸው። |
ስለዚህም ጠላቶቻቸው እነርሱን ድል አድርገው ይገዙአቸው ዘንድ አሳልፈህ ሰጠሃቸው፤ እነርሱም አስጨነቁአቸው። በችግራቸውም ጊዜ ወደ አንተ ጮኹ፤ አንተም በሰማይ ሆነህ ሰማሃቸው፤ ከምሕረትህ ታላቅነት የተነሣ፥ ከጠላቶቻቸው የሚታደጉ መሪዎችን ላክህላቸው።
አቤሜሌክ ከሞተ በኋላ የዶዶ የልጅ ልጅ የፑአ ልጅ ቶላዕ እስራኤልን ለማዳን ተነሣ፤ እርሱም ከይሳኮር ነገድ ሲሆን የሚኖረውም በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ሻሚር ተብላ በምትጠራ ስፍራ ነበር፤
ከዚህ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም ከብንያም ነገድ ግራኝ የነበረውን የጌራን ልጅ ኤሁድን አዳኝ አድርጎ አስነሣቸው፤ የእስራኤል ሕዝብ ኤሁድን ግብር አስይዘው ወደ ሞአብ ንጉሥ ወደ ዔግሎን ላኩት።
ከዚያም ቀጥሎ የነበረው መሪ የዐናት ልጅ ሻምጋር ነበር፤ እርሱም ስድስት መቶ ፍልስጥኤማውያንን በበሬ ቀንድ በመግደል፥ የእስራኤልን ሕዝብ አዳነ።
ይህችም ነቢይት በተራራማው በኤፍሬም አገር በራማና በቤትኤል መካከል በሚገኘው የዲቦራ የተምር ዛፍ ሥር ተቀምጣ ትፈርድ ስለ ነበር የእስራኤል ሕዝብ ፍርድ ለማግኘት ወደ እርስዋ ይሄዱ ነበር።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ሂድ፤ በዚህ ባለህ ብርቱ ኀይል ሁሉ በመጠቀም እስራኤላውያንን ከምድያማውያን እጅ ነጻ አውጣ፤ እነሆ እኔ ራሴ ልኬሃለሁ” ሲል አዘዘው።
በእስራኤል አገር መሳፍንት ይገዙ በነበረበት ዘመን በሀገሩ ላይ ረሀብ ሆነ፤ ከዚህም የተነሣ በይሁዳ ክፍለ ሀገር ከቤተልሔም አንድ ሰው ከሚስቱና ከሁለት ወንዶች ልጆቹ ጋር ለመኖር ወደ ሞአብ አገር ሄደ።
እግዚአብሔርም መጀመሪያ ጌዴዎንን፥ ከዚያም በኋላ ባራቅንና ዮፍታሔን፥ ከዚያም ሶምሶንን፥ በመጨረሻም እኔን ላከ፤ እኛም እያንዳንዳችን እናንተን ከጠላቶቻችሁ አዳናችሁ፤ በሰላምም ኖራችሁ፤