የይሁዳም ሰዎች “በእኛ ላይ አደጋ የምትጥሉት ስለምንድነው?” ሲሉ ጠየቁአቸው። እነርሱም “እኛ የመጣነው ሶምሶንን ልንይዝና እስረኛ አድርገን ወስደን በእኛ ላይ ያደረገውን ሁሉ በእርሱም ላይ ልንፈጽምበት ነው” ሲሉ መለሱላቸው።
መሳፍንት 15:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍልስጥኤማውያን መጥተው በይሁዳ ሰፈሩ፤ ሌሒ ተብላ የምትጠራውንም ከተማ ወረሩአት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍልስጥኤማውያን ወጥተው በይሁዳ ሰፈሩ፤ ከዚያም በሌሒ አጠገብ ተበታትነው አደፈጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍልስጥኤማውያን ወጥተው በይሁዳ ሰፈሩ፤ ከዚያም በሌሒ አጠገብ ተበታትነው አደፈጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍልስጥኤማውያንም ወጡ፤ በይሁዳም ሰፈሩ፤ የአህያ መንጋጋ አጥንት በተባለ ቦታም ተበታትነው ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍልስጥኤማውያንም ወጡ፥ በይሁዳም ሰፈሩ፥ በሌሒ ላይም ተበታትነው ተቀመጡ። |
የይሁዳም ሰዎች “በእኛ ላይ አደጋ የምትጥሉት ስለምንድነው?” ሲሉ ጠየቁአቸው። እነርሱም “እኛ የመጣነው ሶምሶንን ልንይዝና እስረኛ አድርገን ወስደን በእኛ ላይ ያደረገውን ሁሉ በእርሱም ላይ ልንፈጽምበት ነው” ሲሉ መለሱላቸው።
ሶምሶንም ወደ ሌሒ በመጣ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን እየደነፉ መጡበት፤ የእግዚአብሔር መንፈስ አበረታው፤ ክንዱ የታሰሩበት ገመዶች እሳት እንደ ነካቸው የሐር ፈትል ከእጁ ላይ ቀልጠው ወደቁ።
እግዚአብሔር በሌሂ ያለው ጐድጓዳ ቦታ ከፈተለት፤ ከእርሱም ውሃ ወጣ፤ በጠጣም ጊዜ መንፈሱ ተመልሶለት ተጠናከረ፤ ስለዚህም ያ ቦታ “ዐይን ሃቆሬ” የተባለ። እርሱም እስከ ዛሬ ድረስ በሌሂ ይገኛል።