ስለዚህ ትዕማር የመበለትነት ልብሷን ለውጣ ፊቷን በሻሽ ሸፈነች፤ ወደ ቲምና በሚወስደው መንገድ ዳር በዔናይም ደጅ ተቀመጠች፤ ይህንንም ያደረገችው ሴላ አድጎ ሳለ ለእርሱ በሚስትነት እንድትሰጥ አለመፈቀዱን ስለ ተረዳች ነው።
መሳፍንት 15:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሶምሶንንም “አንተ የጠላሃት ስለ መሰለኝ ሚዜህ ለነበረው ሰው ዳርኳት፤ የሆነ ሆኖ የእርስዋ ታናሽ ይበልጥ ውብ አይደለችምን? እባክህ እርስዋን አግባት” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባትየውም፣ “ፈጽሞ የጠላሃት መሆንህን ስለ ተረዳሁ ለሚዜህ ድሬለታለሁ፤ ታናሽ እኅቷ ከርሷ ይልቅ ውብ አይደለችምን? እርሷን አግባት” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባትየውም፥ “ፈጽሞ የጠላሃት መሆንህን ስለ ተረዳሁ ለሚዜህ ድሬለታለሁ፤ ታናሽ እኅቷ ከእርሷ ይልቅ ውብ አይደለችምን? እርሷን አግባት” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቷም፥ “ፈጽመህ ጠላህዋት ያልህ መስሎኝ ለሚዜህ አጋባኋት፤ ታናሽ እኅቷ ከእርስዋ ይልቅ የተዋበች አይደለችምን? እባክህ በእርስዋ ፋንታ አግባት” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባትዋም፦ ፈጽመህ የጠላሃት መስሎኝ ለሚዜህ አጋባኋት፥ ታናሽ እኅትዋ ከርስዋ ይልቅ የተዋበች አይደለችምን? እባክህ፥ በእርስዋ ፋንታ አግባት አለው። |
ስለዚህ ትዕማር የመበለትነት ልብሷን ለውጣ ፊቷን በሻሽ ሸፈነች፤ ወደ ቲምና በሚወስደው መንገድ ዳር በዔናይም ደጅ ተቀመጠች፤ ይህንንም ያደረገችው ሴላ አድጎ ሳለ ለእርሱ በሚስትነት እንድትሰጥ አለመፈቀዱን ስለ ተረዳች ነው።
ስለዚህ የሶምሶን ሚስት እያለቀሰች ወደ እርሱ ቀርባ “ለካስ አንተ እኔን አትወደኝም! እንዲያውም በጣም ትጠላኛለህ! የአገሬን ልጆች እንቆቅልሽ ጠይቀህ ለእኔ እስከ አሁን ፍቺውን አልነገርከኝም!” አለችው። እርሱም “እነሆ! እኔ ይህን ለአባቴና ለእናቴ እንኳ አልነገርኳቸውም፤ ታዲያ ለአንቺ የምነግርበት ምክንያት ምንድን ነው?” አላት።