መሳፍንት 13:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም የማኑሄን ጸሎት ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ እንደገና ወጥቶ ሴቲቱ በእርሻ ውስጥ እንደ ተቀመጠች ተገለጠላት፤ ባልዋ ማኑሄ ከእርስዋ ጋር አልነበረም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም የማኑሄን ጸሎት ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ሴቲቱ በዕርሻ ውስጥ ሳለች ተገለጠላት፤ በዚህ ጊዜ ግን ባሏ ማኑሄ ዐብሯት አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም የማኑሄን ጸሎት ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ሴቲቱ በዕርሻ ውስጥ ሳለች ተገለጠላት፤ በዚህ ጊዜ ግን ባሏ ማኑሄ አብሮአት አልነበረም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም የማኑሄን ቃል ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ እንደ ገና በእርሻ ውስጥ ተቀምጣ ሳለች ወደ ሴቲቱ መጣ፤ ባልዋ ማኑሄ ግን ከእርስዋ ጋር አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የማኑሄን ድምፅ ሰማ፥ የእግዚአብሔርም መልአክ እንደ ገና ለሴቲቱ በእርሻ ውስጥ ተቀምጣ ሳለች ተገለጠላት፥ ባልዋ ማኑሄ ግን ከእርስዋ ጋር አልነበረም። |
ከዚህ በኋላ ማኑሄ “እግዚአብሔር ሆይ! ሕፃኑ ሲወለድ ምን ማድረግ እንደሚገባን ይነግረን ዘንድ ያ የላክኸው የእግዚአብሔር ሰው እንደገና ተመልሶ ወደ እኛ እንዲመጣ አድርግልን” ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።