በአራት እግሮቹ ከሚሄድ እንስሳ በመዳፎቹ ላይ የሚሄድ በእናንተ ዘንድ የረከሰ ይሆናል፤ የእርሱንም በድን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ይሆናል፤
መሳፍንት 13:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወይን ጠጅም ሆነ ማንኛውንም የሚያሰክር መጠጥ ከመጠጣትና ማንኛውንም ርኩስ ምግብ ከመብላት ተጠንቀቂ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ተጠንቀቂ፤ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጪ፤ ርኩስ ነገርም አትብዪ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ተጠንቀቂ፤ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጪ፤ ርኩስ ነገርም አትብይ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ተጠንቀቂ፤ የወይን ጠጅንና የሚያሰክር መጠጥንም አትጠጪ፤ ርኩስም ነገር አትብዪ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም ተጠንቀቂ፥ የወይን ጠጅን የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ። |
በአራት እግሮቹ ከሚሄድ እንስሳ በመዳፎቹ ላይ የሚሄድ በእናንተ ዘንድ የረከሰ ይሆናል፤ የእርሱንም በድን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ይሆናል፤
ንጹሕ በሆነውና ንጹሕ ባልሆነው መካከል ያለውን ልዩነት ለማወቅ፥ ይኸውም በሚበሉትና በማይበሉት እንስሶች መካከል ያለውን ልዩነት ለመረዳት ብርቱ ጥንቃቄ አድርጉ።”
እርሱ በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናል፤ የወይን ጠጅና ሌላም የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገና በእናቱ ማሕፀን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ይሆናል።
ከወይን ተክል የሚገኝ ምንም ነገር መመገብ አይኖርባትም፤ የወይን ጠጅም ሆነ ማንኛውንም የሚያሰክር መጠጥ አትጠጣ፤ ማንኛውንም ርኩስ ምግብ አትበላም፤ በአጠቃላይ እኔ ያዘዝኳትን ሁሉ መፈጸም አለባት።”
ነገር ግን እርሱ ‘እነሆ ትፀንሺአለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ’ ብሎ ነገረኝ፤ እንዲሁም የሚወለደው ልጅ ከተወለደበት ቀን ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ በናዝራዊነት ለእግዚአብሔር የተለየ ስለሚሆን፥ የወይን ጠጅም ሆነ ማንኛውንም የሚያሰክር መጠጥ ከመጠጣትና ማንኛውንም ርኩስ ምግብ ከመብላት እንድጠነቀቅ ነግሮኛል።”