ኢትዮጵያዊ መልኩን፥ ነብርም ዝንጒርጒርነቱን መለወጥ አይችልም፤ እንዲሁም እናንተ ክፉ ነገር ማድረግን ስለ ለመዳችሁ ደግ ሥራ መሥራት አይሆንላችሁም።
መሳፍንት 13:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ እንደገና እግዚአብሔርን በደሉ፤ ስለዚህም አርባ ዓመት ሙሉ እንዲገዙአቸው እግዚአብሔር ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ሰጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን እንደ ገና በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን እጅ አርባ ዓመት እንዲገዙ አሳልፎ ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤላውያን እንደገና በጌታ ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ ስለዚህም ጌታ በፍልስጥኤማውያን እጅ አርባ ዓመት እንዲገዙ አሳልፎ ሰጣቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያን እጅ አርባ ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፥ እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያን እጅ አርባ ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው። |
ኢትዮጵያዊ መልኩን፥ ነብርም ዝንጒርጒርነቱን መለወጥ አይችልም፤ እንዲሁም እናንተ ክፉ ነገር ማድረግን ስለ ለመዳችሁ ደግ ሥራ መሥራት አይሆንላችሁም።
እንግዲህ ሌላ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎን፥ ስለ ባራቅ፥ ስለ ሶምሶን፥ ስለ ዮፍታሔ፥ ስለ ዳዊት፥ ስለ ሳሙኤል፥ ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥረኛል፤
እስራኤላውያን ባዓልና ዐስታሮት የተባሉትን ባዕዳን አማልክት እንዲሁም የሶርያን፥ የሲዶናን፥ የሞአብን፥ የዐሞንንና የፍልስጥኤምን አማልክት በማምለክ እንደገና እግዚአብሔርን በደሉ፤ እርሱንም ማምለክ ተዉ፤
ሶምሶን ይህን እንዲያደርግ የሚመራው እግዚአብሔር እንደ ሆነ ወላጆቹ አላወቁም፤ በዚያም ጊዜ ፍልስጥኤማውያን እስራኤላውያንን ይገዙ ስለ ነበር፥ እግዚአብሔር ፍልስጥኤማውያንን ለመቃወም ምክንያት ይፈልግ ነበር።
ስለዚህም ሦስት ሺህ የሚሆኑ የይሁዳ ሰዎች በዔጣም ወዳለው ዋሻ ሄደው “ፍልስጥኤማውያን ገዢዎቻችን እንደ ሆኑ አታውቅምን? ታዲያ ይህ ያደረግህብን ምንድን ነው?” ሲሉ ሶምሶንን ጠየቁት። እርሱም “እኔ በእነርሱ ላይ ያደረግኹት ልክ እነርሱ በእኔ ላይ ያደረጉትን ነው” አላቸው።
ነገር ግን ሕዝቡ አምላካቸውን እግዚአብሔርን ረሱ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የሓጾር ሠራዊት አዛዥ ለነበረው ለሲሣራ፥ ለፍልስጥኤማውያን፥ ለሞአብም ንጉሥ አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም እስራኤላውያንን ድል ነሡ።
ፍልስጥኤማውያን ሆይ! እንግዲህ በርቱ! ጠንክሩ! ይህ ካልሆነ ቀድሞ እነርሱ የእኛ ባሪያዎች እንደ ነበሩ ሁሉ እኛም ደግሞ የዕብራውያን ባርያዎች ሆነን መቅረታችን ነው፤ ስለዚህ በወንድነት ጠንክራችሁ ተዋጉ!”
በዚህም ዐይነት ፍልስጥኤማውያን ድል ተመቱ። ሳሙኤል በኖረበት ዘመን ሁሉ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ስለ ነበረ ፍልስጥኤማውያን ዳግመኛ ወደ እስራኤል ድንበር አልቀረቡም።