መሳፍንት 12:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢብጻን ሠላሳ ወንዶችና ሠላሳ ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ሴቶች ልጆቹን ከጐሣው ውጪ ከሆኑ ወንዶች ጋር አጋባቸው፤ እንዲሁም ከጐሣው ውጪ የሆኑ ሴቶች ልጆችን አምጥቶ ከወንዶች ልጆቹ ጋር እንዲጋቡ አደረገ፤ ኢብጻን ሰባት ዓመት የእስራኤል መሪ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ሠላሳ ወንዶችና ሠላሳ ሴቶች ልጆች ነበሩት። ሴቶች ልጆቹንም ከጐሣው ውጭ ለሆኑ ሰዎች ዳራቸው፤ ከጐሣው ውጭ የሆኑ ሠላሳ ልጃገረዶች አምጥቶ ከወንዶች ልጆቹ ጋራ አጋባቸው። ኢብጻን በእስራኤል ላይ ሰባት ዓመት ፈራጅ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ሠላሳ ወንዶችና ሠላሳ ሴቶች ልጆች ነበሩት። ሴቶች ልጆቹንም ከጐሣው ውጭ ለሆኑ ሰዎች ዳራቸው፤ ጐሣው ውጭ የሆኑ ሠላሳ ልጃገረዶች አምጥቶ ከወንዶች ልጆቹ ጋር አጋባቸው። ኢብጻን በእስራኤል ላይ ሰባት ዓመት ፈራጅ ሆነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሠላሳ ወንዶች ልጆችና ሠላሳ ሴቶች ልጆችንም ወለደ፤ ሠላሳ ሴቶች ልጆቹንም ወደ ውጭ ሀገር ዳረ፤ ለወንዶች ልጆቹም ከውጭ ሀገር ሠላሳ ሴቶች ልጆችን አመጣ። እስራኤልንም ሰባት ዓመት ገዛ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሠላሳም ወንዶች ልጆችና ሠላሳ ሴቶች ልጆች ነበሩት፥ ሠላሳ ሴቶች ልጆቹንም ወደ ውጭ አገር ዳረ፥ ለወንዶች ልጆቹም ከውጭ አገር ሴቶች ልጆችን አመጣ። በእስራኤልም ላይ ሰባት ዓመት ፈረደ። |
በሠላሳ አህዮች ላይ ተቀምጠው የሚጋልቡ ሠላሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም በገለዓድ ምድር ሠላሳ ከተሞች ነበሩአቸው፤ እነዚህም ከተሞች እስከ ዛሬ የያኢር መንደሮች ተብለው ይጠራሉ፤
ዓብዶን በሰባ አህዮች ላይ ተቀምጠው የሚጋልቡ አርባ ወንዶች ልጆችና ሠላሳ የልጅ ልጆች ነበሩት፤ ዓብዶን ስምንት ዓመት የእስራኤል መሪ ሆነ።