የኤፍሬም ሰዎች ለጦርነት ተዘጋጅተው የዮርዳኖስን ወንዝ በመሻገር ወደ ጻፎን በደረሱ ጊዜ ዮፍታሔን “ዐሞናውያንን ለመውጋት ወሰን አልፈህ ስትሄድ እኛን ያልጠራኸን ለምንድን ነው? እንግዲህ እኛም ቤትህን በላይህ እናቃጥለዋለን!” አሉት።
መሳፍንት 12:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮፍታሔም እንዲህ አላቸው፤ “እኔና ሕዝቤ ከዐሞናውያን ጋር በብርቱ ተጣልተን በነበረበት ጊዜ እናንተን ጠርቼአችሁ ነበር፤ ነገር ግን ከእነርሱ ጥቃት አላዳናችሁኝም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮፍታሔም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “እኔና ሕዝቤ ከአሞናውያን ጋራ ከፍተኛ ትግል ገጥመን በነበረበት ጊዜ ጠርቼያችሁ ከእጃቸው አላዳናችሁኝም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮፍታሔም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “እኔና ሕዝቤ ከአሞናውያን ጋር ከፍተኛ ትግል ገጥመን በነበረበት ጊዜ ጠርቼያችሁ ከእጃቸው አላዳናችሁኝም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮፍታሔም፥ “እኔና ሕዝቤ የተገፋን ነን፤ የአሞን ልጆችም በጽኑዕ አሠቃዩን፤ በጠራናችሁም ጊዜ ከእጃቸው አላዳናችሁንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮፍታሔም፦ ከአሞን ልጆች ጋር ለእኔና ለሕዝቤ ጽኑ ጠብ ነበረን፥ በጠራኋችሁም ጊዜ ከእጃቸው አላዳናችሁኝም። |
የኤፍሬም ሰዎች ለጦርነት ተዘጋጅተው የዮርዳኖስን ወንዝ በመሻገር ወደ ጻፎን በደረሱ ጊዜ ዮፍታሔን “ዐሞናውያንን ለመውጋት ወሰን አልፈህ ስትሄድ እኛን ያልጠራኸን ለምንድን ነው? እንግዲህ እኛም ቤትህን በላይህ እናቃጥለዋለን!” አሉት።
እናንተ እኔን ለመርዳት አለመፈለጋችሁን ባየሁ ጊዜ ለሕይወቴ ሳልሳሳ እነርሱን ለመውጋት ወሰኑን ተሻግሬ ሄድሁ፤ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ድልን አቀዳጀኝ። ታዲያ፥ አሁን እኔን ለመውጋት የተነሣችሁበት ምክንያት ምንድን ነው?”