ዐሞናውያን ዳዊትን በገዛ እጃቸው ጠላት እንዳደረጉት ተገነዘቡ፤ ስለዚህም እግረኛ ወታደሮችን ከቤትረሖብና ከጾባ ኻያ ሺህ ሶርያውያንንና ከጦብ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችን፤ እንዲሁም ከንጉሥ ማዕካ አንድ ሺህ ሰዎችን ቀጠሩ፤
መሳፍንት 11:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም በሆነ ጊዜ የገለዓድ መሪዎች ዮፍታሔን ከጦብ ምድር መልሰው ለማምጣት ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የገለዓድ አለቆች ዮፍታሔን ለማምጣት ወደ ጦብ ምድር ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የገለዓድ አለቆች ዮፍታሔን ለማምጣት ወደ ጦብ ምድር ሄዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የገለዓድ ሽማግሌዎችም ዮፍታሔን ከጦብ ምድር ለማምጣት ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሞንም ልጆች ከእስራኤል ጋር በተዋጉ ጊዜ የገለዓድ ሽማግሌዎች ዮፍታሔን ከጦብ ምድር ለማምጣት ሄዱ። |
ዐሞናውያን ዳዊትን በገዛ እጃቸው ጠላት እንዳደረጉት ተገነዘቡ፤ ስለዚህም እግረኛ ወታደሮችን ከቤትረሖብና ከጾባ ኻያ ሺህ ሶርያውያንንና ከጦብ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችን፤ እንዲሁም ከንጉሥ ማዕካ አንድ ሺህ ሰዎችን ቀጠሩ፤
ዐሞናውያን ተሰልፈው ወጥተው የእነርሱ ዋና ከተማቸው በሆነችው በራባ መግቢያ በር አጠገብ ስፍራቸውን ያዙ፤ ሌሎቹ ሶርያውያን፥ ከጦብና ከማዕካ የመጡት ጦረኞች በአንድ ሜዳማ ቦታ ስፍራቸውን ያዙ።
ነገር ግን አንዳንድ ሥርዓተ አልባዎች “አሁን ይህ ሰው እኛን ለማዳን ይችላል?” ተባባሉ፤ እርሱንም በመናቅ ምንም ዐይነት ገጸ በረከት ሳያመጡለት ቀሩ። ሳኦል ግን ዝም አለ።
ከዚህ በኋላ ሕዝቡ ሳሙኤልን “ሳኦል በእኛ ላይ አይነግሥብንም ያሉት ሰዎች እነማን ናቸው? እነርሱን አሳልፈህ ስጠንና እንግደላቸው!” አሉት።