ስለዚህ ይህ በደላችሁ ተሰነጣጥቆ በማኰፍኰፍ ሊወድቅ እንደ ተቃረበና አወዳደቁም በፍጥነትና በቅጽበት እንደሚደርስበት እንደ ረጅም የቅጽር ግንብ ያደርጋችኋል።
መሳፍንት 10:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሞናውያንና ፍልስጥኤማውያንም ከዮርዳኖስ ማዶ በአሞራውያን ምድር በገለዓድ ውስጥ የሚኖሩትን እስራኤላውያንን ለዐሥራ ስምንት ዓመት አስጨንቀው ገዙአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም በዚያ ዓመት ሰበሯቸው፤ አደቀቋቸውም፤ ለዐሥራ ስምንት ዓመታት ከዮርዳኖስ ማዶ ባለው የአሞራውያን ምድር፣ በገለዓድ የነበሩትን እስራኤላውያንን ሁሉ አሠቃዩአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ዓመት የእስራኤልን ልጆች ሥቃይ አበዙባቸው፥ በዮርዳኖስ ማዶ በአሞራውያን አገር በገለዓድ ውስጥ ያሉትን የእስራኤልን ልጆች ሁሉ ዐሥራ ስምንት ዓመት ተጋፉአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ጊዜ የእስራኤልን ልጆች ሥቃይ አበዙባቸው፤ በዮርዳኖስ ማዶ በአሞሬዎናውያን ሀገር በገለዓድ ውስጥ ያሉትን የእስራኤልን ልጆች ሁሉ ዐሥራ ስምንት ዓመት አስጨነቁአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ዓመት የእስራኤልን ልጆች ሥቃይ አበዙባቸው፥ በዮርዳኖስ ማዶ በአሞራውያን አገር በገለዓድ ውስጥ ያሉትን የእስራኤልን ልጆች ሁሉ አሥራ ስምንት ዓመት ተጋፉአቸው። |
ስለዚህ ይህ በደላችሁ ተሰነጣጥቆ በማኰፍኰፍ ሊወድቅ እንደ ተቃረበና አወዳደቁም በፍጥነትና በቅጽበት እንደሚደርስበት እንደ ረጅም የቅጽር ግንብ ያደርጋችኋል።
ሰዎች “ሁሉ ነገር ሰላምና የተረጋጋ ነው” ሲሉ እርጉዝ ሴትን ምጥ እንደሚይዛት ዐይነት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ በምንም ዐይነት አያመልጡም።