መሳፍንት 10:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከቶላዕ ቀጥሎ ገለዓዳዊው ያኢር ተነሣ፤ እርሱም ኻያ ሁለት ዓመት የእስራኤል መሪ ሆነ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከቶላ ቀጥሎ ገለዓዳዊው ኢያዕር ተነሣ፤ እርሱም በእስራኤል ላይ ሃያ ሁለት ዓመት በፈራጅነት ተቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከቶላ ቀጥሎ ገለዓዳዊው ያኢር ተነሣ፤ እርሱም በእስራኤል ላይ ሃያ ሁለት ዓመት በፈራጅነት ተቀመጠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱም በኋላ ገለዓዳዊዉ ኢያዕር ተነሣ፤ እስራኤልንም ሃያ ሁለት ዓመት ገዛ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም በኋላ ገለዓዳዊው ኢያዕር ተነሣ፥ በእስራኤልም ላይ ሀያ ሁለት ዓመት ፈረደ። |
“የጋድና የሮቤል ሰዎች ዮርዳኖስን ተሻግረው በእግዚአብሔር መሪነት ለጦርነት የሚዘጋጁ ከሆነና በእነርሱም ርዳታ ምድሪቱን የምትወርሱ ከሆነ የገለዓድን ምድር ለእነርሱ ርስት አድርጋችሁ ስጡአቸው።
በሠላሳ አህዮች ላይ ተቀምጠው የሚጋልቡ ሠላሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም በገለዓድ ምድር ሠላሳ ከተሞች ነበሩአቸው፤ እነዚህም ከተሞች እስከ ዛሬ የያኢር መንደሮች ተብለው ይጠራሉ፤