ከዚህም የተነሣ በአብራም እረኞችና በሎጥ እረኞች መካከል ጠብ ተነሣ፤ በዚያን ዘመን የዚያች ምድር ነዋሪዎች ከነዓናውያንና ፈሪዛውያን ነበሩ።
መሳፍንት 1:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም አዶኒቤዜቅን በቤዜቅ አግኝተው ከእርሱ ጋር ጦርነት ገጠሙ፤ ከነዓናውያንንና ፈሩዛውያንን ድል አደረጉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህም አዶኒቤዜቅን አግኝተው ተዋጉት፤ ከነዓናውያንንና ፌርዛውያንን ድል አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አዶኒቤዜቅንም በቤዜቅ አገኙትና ተዋጉት፤ ከነዓናውያንንና ፌርዛውያንን ድል አደረጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አዶኒቤዜቅንም በቤዜቅ አገኙትና ተዋጉት፤ ከነዓናውያንንና ፌርዜዎናውያንንም ገደሉአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አዶኒቤዜቅንም በቤዜቅ አገኙትና ተዋጉት፥ ከነዓናውያንንና ፌርዛውያንንም መቱአቸው። |
ከዚህም የተነሣ በአብራም እረኞችና በሎጥ እረኞች መካከል ጠብ ተነሣ፤ በዚያን ዘመን የዚያች ምድር ነዋሪዎች ከነዓናውያንና ፈሪዛውያን ነበሩ።
ከዚያ በኋላ የይሁዳ ሕዝብ አብሮ ዘመተ። እግዚአብሔርም በከነዓናውያንና በፈሪዛውያን ላይ ድልን አቀዳጃቸው፤ እነርሱም በቤዜቅ ዐሥር ሺህ ሠራዊትን መቱ።