ሚክያስም ወደ ንጉሥ አክዓብ ፊት በቀረበ ጊዜ ንጉሡ “ሚክያስ ሆይ! ንጉሥ ኢዮሣፍጥና እኔ ወደ ራሞት ሄደን ጦርነት እንክፈት ወይስ እንተው?” ሲል ጠየቀው። ሚክያስም “ዘምተህ አደጋ ጣልባት! በእርግጥም ታሸንፋለህ፤ እግዚአብሔርም ድልን ያቀዳጅሃል” ሲል መለሰለት።
መሳፍንት 1:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ በኋላ የይሁዳ ሕዝብ አብሮ ዘመተ። እግዚአብሔርም በከነዓናውያንና በፈሪዛውያን ላይ ድልን አቀዳጃቸው፤ እነርሱም በቤዜቅ ዐሥር ሺህ ሠራዊትን መቱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁዳ በከነዓናውያንና በፌርዛውያን ላይ ወጣ፤ እግዚአብሔርም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው፤ ቤዜቅ በተባለውም ስፍራ ዐሥር ሺሕ ሰው ገደሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያ በኋላ ይሁዳ ሕዝብ ዘመተ፤ ጌታም ከነዓናውያንንና ፌርዛውያንን በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው፤ በቤዜቅም ዐሥር ሺህውን ድል ነሡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይሁዳም ወጣ፤ እግዚአብሔርም ከነዓናውያንንና ፌርዜዎናውያንን በእጁ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ከእነርሱም በቤዜቅ ውስጥ ዐሥር ሺህ ሰዎችን ገደለባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሁዳም ወጣ፥ እግዚአብሔርም ከነዓናውያንንና ፌርዛውያንን በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው፥ ከእነርሱም በቤዜቅ ውስጥ አሥር ሺህ ሰዎች ገደሉ። |
ሚክያስም ወደ ንጉሥ አክዓብ ፊት በቀረበ ጊዜ ንጉሡ “ሚክያስ ሆይ! ንጉሥ ኢዮሣፍጥና እኔ ወደ ራሞት ሄደን ጦርነት እንክፈት ወይስ እንተው?” ሲል ጠየቀው። ሚክያስም “ዘምተህ አደጋ ጣልባት! በእርግጥም ታሸንፋለህ፤ እግዚአብሔርም ድልን ያቀዳጅሃል” ሲል መለሰለት።
ስለዚህ አክዓብ አራት መቶ የሚሆኑትን ነቢያቱን ጠርቶ “ወደ ራሞት ሄጄ አደጋ ልጣልባት ወይስ ልተው?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም “ሄደህ አደጋ ጣልባት፤ ጌታም ድልን ያቀዳጅሃል” ሲሉ መለሱለት።
በቀድሞ ዘመን እጆችህ ያደረጉትን ድርጊት ሁሉ አባቶቻችን ነግረውናል፤ ይኸውም፥ እነርሱን ለመትከል ሕዝቦችን አባረሃል፤ እነርሱን ለማደላደል ነዋሪዎቹን አጥፍተሃል።
እግዚአብሔር አምላክህ እነዚህን ሁሉ ሕዝቦች ለእናንተ አሳልፎ ሲሰጣቸውና እነርሱን ድል በምትነሣበት ጊዜ ሁሉንም መደምሰስ አለብህ፤ ከእነርሱ ጋር ምንም ዐይነት ውል አታድርግ፤ አትራራላቸውም።
ነገር ግን እንደሚባላ እሳት የሆነ እግዚአብሔር አምላክህ በፊትህ የሚሄድ መሆኑን ዛሬ ታያለህ፤ አንተ ወደ ፊት በሄድህ መጠን እርሱ ድል ይነሣቸዋል፤ ስለዚህም እርሱ በሰጠው ተስፋ መሠረት እነርሱን ነቃቅለህ በማባረር በፍጥነት ታጠፋቸዋለህ።
የይሁዳ ነገድ ሕዝቦች ወንድሞቻቸውን የስምዖንን ነገድ ሕዝቦች “ለእኛ ወደ ተደለደለው ርስት በከነዓናውያን ላይ ለመዝመት ከእኛ ጋር አብረን እንሂድ እኛም ለእናንተ ወደተደለደለው ርስት አብረን እንሄዳለን” አሉአቸው። የስምዖን ነገድ ሕዝቦች ከእነርሱ ጋር ሄዱ።
ነገር ግን ‘ወደ እኛ ኑ’ ቢሉን፥ ወደ እነርሱ እንሄዳለን፤ ይህም እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ላይ ድልን የሚያቀዳጀን ለመሆኑ ምልክት ይሆንልናል።”
ዮናታን ጋሻ ጃግሬ የሆነውን ወጣት “ና ወደ እነዚያ ወደ አልተገረዙት ወገኖች የጦር ሰፈር እንሻገር እግዚአብሔር ይረዳን ይሆናል፤ በብዙም ሆነ በጥቂት እግዚአብሔር ማዳን አይሳነውም” አለው።