መሳፍንት 1:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሙሴ ዐማት የነበረው የቄናዊው ዘሮች ከይሁዳ ሕዝብ ጋር በመሆን የተምር ዛፎች ከሞሉባት ከኢያሪኮ ከተማ ተነሥተው፥ በይሁዳ ካለችው ከዐራድ በስተደቡብ ወዳለው ደረቅ ምድር ተጓዙ፤ እዚያም በዐማሌቃውያን መካከል ተቀመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቄናዊው የሙሴ ዐማት ዝርያዎች ከዓራድ አጠገብ በኔጌብ ውስጥ በይሁዳ ምድረ በዳ ካሉት ሕዝቦች ጋራ ዐብረው ለመኖር፣ ከይሁዳ ሰዎች ጋራ በመሆን ከባለ ዘንባባዋ ከተማ ከኢያሪኮ ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቄናዊው የሙሴ አማት ዘሮች ከይሁዳ ሰዎች ጋር በመሆን ከዘንባባዋ ከተማ ተነሥተው፥ ዓራድ አጠገብ በኔጌብ ውስጥ በይሁዳ ምድረ በዳ ካሉት ሕዝቦች ጋር አብረው ሄዱ፥ እዚያም ከሕዝቡ ጋር ተቀመጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቄናዊው የሙሴ አማት የዮባብ ልጆችም ከዘንባባ ከተማ ተነሥተው ከዓራድ በአዜብ በኩል ወዳለው ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ ወደ ይሁዳ ልጆች ሄደው ከሕዝቡ ጋር ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቄናዊው የሙሴ አማት ልጆችም ከይሁዳ ልጆች ጋር ዘንባባ ካለበት ከተማ ተነሥተው ከዓራድ በደቡብ በኩል ወዳለው ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ ወጡ፥ ሄደውም ከሕዝቡ ጋር ተቀመጡ። |
ቲርዓውያን፥ ሺምዓውያንና ሱካውያን የተባሉት ታሪክ በመጻፍና በመገልበጥ ጥበበኞች የነበሩት ጐሣዎች ያዕቤጽ ተብላ በምትጠራ ትንሽ ከተማ ይኖሩ ነበር፤ እነርሱም ከሬካባውያን አባት ከሐሜት የወጡ ቄናውያን ነበሩ።
ኤዶማውያን የይሁዳን ግዛት እንደገና በመውረር ብዙ ሰዎችን ማርከው ወሰዱ፤ ስለዚህ ንጉሥ አካዝ ርዳታ እንዲልክለት የአሦርን ንጉሠ ነገሥት ለመነ።
የምድያም ካህን የሆነው የሙሴ ዐማት የትሮ፥ እግዚአብሔር ከግብጽ ምድር መርቶ ባወጣቸው ጊዜ ለሙሴና ለእስራኤል ሕዝብ ያደረገላቸውን ነገር ሁሉ ሰማ፤
ከዚህም በኋላ የትሮ የሙሴ ዐማት በሙሉ የሚቃጠል ቊርባንና ሌላም ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት አመጣ፤ አሮንና የእስራኤል አለቆችም ሁሉ የተቀደሰውን ምግብ በአምልኮት ሥርዓት በእግዚአብሔር ፊት ለመመገብ ከሙሴ ዐማት ጋር መጡ።
እነሆ፥ ሙሴ የምድያም ካህን የሆነውን የዐማቹን የየትሮንን በጎች ይጠብቅ ነበር፤ መንጋውንም እየነዳ ከበረሓው ማዶ ወዳለው የእግዚአብሔር ተራራ እየተባለ ወደሚጠራው ወደ ሲና መጣ።
ሙሴም ወደ ዐማቱ ወደ የትሮ ተመልሶ ሄደና “በግብጽ ወደሚኖሩት ወገኖቼ ተመልሼ ሄጄ በሕይወት መኖራቸውን እንዳይ ፍቀድልኝ” አለው። የትሮም ፈቅዶ “በሰላም ሂድ” አለው።
“ወደ ሬካባውያን ቤተሰብ አባሎች ሂድና አነጋግራቸው፤ ከዚያም በኋላ በቤተ መቅደስ ካሉት ክፍሎች ወደ አንዱ አስገብተህ የሚጠጡት የወይን ጠጅ አቅርብላቸው፤”
መኖሪያው ኔጌብ የነበረ የከነዓናውያን ንጉሥ ዐራድ እስራኤላውያን በአታሪም በኩል መምጣታቸውን በሰማ ጊዜ በእነርሱ ላይ አደጋ ጥሎ ጥቂቶቹን ማረከ።
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለዘሮቻቸው አወርሳት ዘንድ ለአብርሃም ለይስሐቅና ለያዕቆብ በመሐላ ቃል የገባሁላቸው የተስፋ ምድር ይህች ናት፤ እነሆ፥ እርስዋን በዐይንህ እንድታያት አድርጌአለሁ፤ ወደዚያች መግባት ግን አይፈቀድልህም።”
እርስዋም “የሰጠኸኝ መሬት በረሓማ ላይ ስለ ሆነ ጥቂት የውሃ ምንጮች እንድትሰጠኝ እለምንሃለሁ፤” አለችው፤ ስለዚህ ካሌብ የላይኛውንና የታችኛውን ምንጮች ሰጣት።
ቀኔናዊው ሔቤር የሙሴ ዐማት ከነበረው ከሆባብ ልጆች ከቄናውያን ተለየ፤ ወደ ቃዴስ ቀረብ ብሎ በጸእናይም በሚገኘው በታላቁ ዛፍ አጠገብ ድንኳኑን ተከለ።
የሐጾር ንጉሥ ያቢን ከሔቤር ቤተሰብ ጋር ሰላም መሥርቶ ይኖር ስለ ነበር ሲሣራ ሸሽቶ የቄናዊው የሔቤር ሚስት ወደሆነችው ወደ ያዔል ድንኳን ገባ።
“እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ ጊዜ ቸርነት ስላደረጋችሁላቸው እናንተን ከአማሌቃውያን ጋር እንዳላጠፋ ከዐማሌቃውያን ተለይታችሁ ሂዱ” ብሎ ሳኦል ለቄናውያን ነገራቸው። እነርሱም ከዐማሌቃውያን ተለይተው ሄዱ።
አኪሽ “በዚህ ጊዜ ወረራ ያደረጋችኹት በየት በኩል ነው” ብሎ ሲጠይቀው ዳዊት “እኛ የዘመትነው ከይሁዳ በስተ ደቡብ ባለው ክፍል፥ እንደገናም በይራሕመኤል ነገድ ግዛትና ቄናውያን በሚኖሩበት ግዛት ነው” እያለ ይመልስለት ነበር።